Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 8:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እር​ሱም “እም​ነ​ታ​ችሁ ወዴት አለ?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ፈር​ተው ተደ​ነቁ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ውኃም ነፋ​ስም የሚ​ታ​ዘ​ዙ​ለት ይህ ማነው?” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እርሱም ደቀ መዛሙርቱን፣ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። እነርሱም በፍርሀትና በመደነቅ፣ “ይህ ነፋስንና ውሃን የሚያዝዝ፣ እነርሱም የሚታዘዙለት እርሱ ማን ነው?” ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እርሱም፦ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። በፍርሃትና በመደነቅ ተውጠውም፤ እርስ በርሳቸው፦ “እንዲህ ነፋሳትንና ውኃን ሳይቀር የሚያዝ፥ እነርሱም የሚታዘዙለት ይህ ለመሆኑ ማን ነው?” ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፥ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። እነርሱ ግን እጅግ ተደንቀውና ፈርተው እርስ በርሳቸው፥ “ነፋስንና ማዕበልን ያዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል፤ ለመሆኑ ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እርሱም፦ እምነታችሁ የት ነው? አላቸው። ፈርተውም ተደነቁ፥ እርስ በርሳቸውም፦ እንዲህ ነፋሳትንና ውኃን እንኳ የሚያዝ ለእርሱም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 8:25
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ስለ ምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።


ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና “አንተ እምነት የጎደለህ፤ ስለምን ተጠራጠርህ?” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ብታ​ም​ናስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ታያ​ለሽ አላ​ል​ሁ​ሽም ነበ​ርን?” አላት።


እነሆ፥ ዛሬ ያለ​ውን፥ ነገም ወደ እሳት የሚ​ጣ​ለ​ውን የአ​በባ አገዳ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ከሆነ፥ እና​ንተ እም​ነት የጐ​ደ​ላ​ችሁ፥ ለእ​ና​ን​ተማ እን​ዴት አብ​ልጦ አያ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ?


ኢየሱስም “ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ ‘ከዚህ ወደዚያ እለፍ፤’ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።


ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ ውኃ ከትእዛዙ እንዳያልፍ፥ የምድርን መሠረት ባጸና ጊዜ፥


እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?


ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ “እውነት እላችኋለሁ፤ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም።


በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ “ወደ ማዶ እንሻገር፤” አላቸው።


ቀር​በ​ውም፥ “መም​ህር ሆይ፥ መም​ህር ሆይ፥ ልን​ጠፋ ነው” ብለው ቀሰ​ቀ​ሱት፤ ተነ​ሥ​ቶም ነፋ​ሱ​ንና የው​ኃ​ዉን ማዕ​በል ገሠ​ጻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ታላቅ ፀጥ​ታም ሆነ።


ከዚህ በኋላ በገ​ሊላ ወደብ አቅ​ጣጫ ወዳ​ለ​ችው ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ኖን ሀገር በታ​ንኳ ሄዱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች