Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 7:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እኔም ወደ አንተ ልመጣ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ነገር ግን በቃ​ልህ እዘዝ፤ ብላ​ቴ​ና​ዬም ይድ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚህም የተነሣ በአንተ ፊት ለመቅረብ እንኳ እንደሚገባኝ ራሴን አልቈጠርሁም፤ ብቻ አንድ ቃል ተናገር፤ ብላቴናዬም ይፈወሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ወደ አንተም ለመምጣት እንኳ ራሴን የተገባሁ አድርጌ አልቆጠርሁትም፤ ነገር ግን አንዲት ቃል ተናገር፤ አገልጋዬም ይፈወሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እኔም ራሴ ወደ አንተ ለመምጣት የበቃሁ ሰው አይደለሁም። ስለዚህ አንተ እዚያው ሆነህ አንድ ቃል ተናገር፤ አገልጋዬም ይድናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ስለዚህም ወደ አንተ ልመጣ እንዲገባኝ ሰውነቴን አልቈጠርሁትም፤ ነገር ግን ቃል ተናገር፥ ብላቴናዬም ይፈወሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 7:7
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለሚ​ፈ​ሩት ችግር የለ​ባ​ቸ​ው​ምና ቅዱ​ሳን ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩት።


እር​ሱም፥ “አንተ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አጥ​ብ​ቀህ ብት​ሰማ፥ በፊ​ቱም መል​ካ​ምን ብታ​ደ​ርግ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ብታ​ደ​ምጥ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ያመ​ጣ​ሁ​ትን በሽታ አላ​ደ​ር​ስ​ብ​ህም፤ እኔ ፈዋ​ሽህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና” አለ።


ሁሉም “ይህ ምንድር ነው? በሥልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው?” ብለው እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ።


ሁሉም ደነ​ገጡ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተነ​ጋ​ገሩ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ይህ ነገር ምን​ድን ነው? ክፉ​ዎ​ችን አጋ​ን​ንት በሥ​ል​ጣ​ንና በኀ​ይል ያዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፥ እነ​ር​ሱም ይወ​ጣ​ሉና።”


እጁ​ንም ዘር​ግቶ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “እወ​ዳ​ለሁ ንጻ” አለው፤ ያን​ጊ​ዜም ለምጹ ለቀ​ቀው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሄደ፤ ወደ ቤቱም በቀ​ረበ ጊዜ፥ የመቶ አለ​ቃዉ ወዳ​ጆ​ቹን እን​ዲህ ብሎ ላከ፥ “አቤቱ፥ አት​ድ​ከም፤ ከቤቴ ጣራ በታች ልት​ገባ አይ​ገ​ባ​ኝ​ምና።


እኔም እኮ ገዢ ሰው ነኝ፤ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሉኝ፤ አን​ዱን ሂድ ብለው ይሄ​ዳል፤ ሌላ​ው​ንም ና ብለው ይመ​ጣል፤ አገ​ል​ጋ​ዬ​ንም እን​ዲህ አድ​ርግ ብለው ያደ​ር​ጋል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ አድ​ን​ማ​ለሁ፤ እኔ እገ​ር​ፋ​ለሁ፤ ይቅ​ርም እላ​ለሁ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ድ​ላል፤ ያድ​ና​ልም፤ ወደ ሲኦል ያወ​ር​ዳል፤ ያወ​ጣ​ልም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች