Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 7:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ስም​ዖን ሆይ፥ የም​ነ​ግ​ርህ ነገር አለኝ” አለው፤ እር​ሱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ተና​ገር” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ኢየሱስም፣ “ስምዖን ሆይ፤ የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። እርሱም፣ “መምህር ሆይ፤ ንገረኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ኢየሱስም መልሶ፦ “ስምዖን ሆይ! አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ፤” አለው። እርሱም፦ “መምህር ሆይ! ተናገር፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ኢየሱስም፦ “ስምዖን ሆይ፥ አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ፤” አለው። እርሱም፦ “መምህር ሆይ! እሺ ንገረኝ!” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ኢየሱስም መልሶ፦ ስምዖን ሆይ፥ የምነግርህ ነገር አለኝ አለው። እርሱም፦ መምህር ሆይ፥ ተናገር አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 7:40
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁን አንተ ሁሉን እን​ደ​ም​ታ​ውቅ፥ ማንም ሊነ​ግ​ርህ እን​ደ​ማ​ትሻ ዐወ​ቅን፤ በዚ​ህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣህ እና​ም​ና​ለን።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሊጠ​ይ​ቁት እን​ደ​ሚሹ ዐውቆ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ” ስለ አል​ኋ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ነገር እርስ በር​ሳ​ችሁ ትመ​ራ​መ​ራ​ላ​ች​ሁን?


እና​ንተ ‘መም​ህ​ራ​ችን፥ ጌታ​ች​ንም’ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ፤ መል​ካም ትላ​ላ​ችሁ፤ እኔ እን​ዲሁ ነኝና።


እር​ሱም በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “መም​ህር ሆይ፥ ልታ​ስ​ተ​ምር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ መጣህ እና​ው​ቃ​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ይህን ተአ​ምር ሊያ​ደ​ርግ የሚ​ችል የለ​ምና።”


አንድ አለ​ቃም፥ “ቸር መም​ህር፥ ምን ሥራ ሠርቼ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እወ​ር​ሳ​ለሁ?” አለው።


እርሱ ግን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ያው​ቅ​ባ​ቸው ነበ​ርና እጁ የሰ​ለ​ለ​ች​ውን ሰው፥ “ተነ​ሥ​ተህ በመ​ካ​ከል ቁም” አለው፤ ተነ​ሥ​ቶም ቆመ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ባለ መድ​ኀ​ኒ​ትን በሽ​ተ​ኞች እንጂ ጤነ​ኞች አይ​ሹ​ትም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በል​ባ​ችሁ ምን ታስ​ባ​ላ​ችሁ?


በዚያ ቀን ብዙዎች ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን?’ ይሉኛል።


ሕዝብ እን​ደ​ሚ​መጣ ወደ አንተ ይመ​ጣሉ፤ እንደ ሕዝ​ቤም በፊ​ትህ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ቃል​ህ​ንም ይሰ​ማሉ፤ ነገር ግን አያ​ደ​ር​ጉ​ትም፤ በአ​ፋ​ቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባ​ቸ​ውም ጣዖ​ታ​ትን ይከ​ተ​ላ​ልና።


ወዲያውም ወደ ኢየሱስ ቀረበና “መምህር ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤” ብሎ ሳመው።


እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፣ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል።


የጠ​ራው ፈሪ​ሳ​ዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የም​ት​ዳ​ስ​ሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እን​ዴ​ትስ እንደ ነበ​ረች ባላ​ወ​ቀም ነበ​ርን? ኀጢ​አ​ተኛ ናትና።”


እር​ሱም እን​ዲህ አለው፥ “ለአ​ንድ አበ​ዳሪ ሁለት ባለ ዕዳ​ዎች ነበ​ሩት፤ በአ​ንዱ አም​ስት መቶ ዲናር ነበ​ረ​በት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም አምሳ።


ደግ​ሞም፥ “ከአ​ንቺ ጋር ጉዳይ አለኝ” አለ፤ እር​ስ​ዋም፥ “ተና​ገር” አለ​ችው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች