Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 7:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 የሰው ልጅም እየ​በ​ላና እየ​ጠጣ መጣ፤ እና​ንተ ግን እነሆ፥ በላ​ተ​ኛና ወይን ጠጪ ሰው፥ የኃ​ጥ​ኣ​ንና የቀ​ራ​ጮች ወዳጅ አላ​ች​ሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፣ ‘በልቶ የማይጠገብና ጠጪ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ አላችሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እናንተም “እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፤ የቀራጮችና የኀጢአተኞች ወዳጅ ነው፤” አላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 የሰው ልጅ ደግሞ እየበላና እየጠጣ ቢመጣ፥ ‘እነሆ፥ ይህ መብልና መጠጥ የሚወድ ነው፤ የቀራጮችና የኃጢአተኞችም ወዳጅ ነው፥’ አላችሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጥቶአልና፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ አላችሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 7:34
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “ይህስ ኀጢ​ኣ​ተ​ኞ​ችን ይቀ​በ​ላል፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ይበ​ላል” ብለው አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


በዚ​ያም ምሳ አደ​ረ​ጉ​ለት፤ ማር​ታም ታሳ​ል​ፍ​ላ​ቸው ነበር፤ አብ​ረ​ውት ምሳ ከበ​ሉ​ትም አንዱ አል​ዓ​ዛር ነበር።


ሁሉም አይ​ተው “ወደ ኀጢ​ኣ​ተኛ ሰው ቤት ሊውል ገባ” ብለው አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


ከዚ​ህም በኋላ ሄዶ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን አለ​ቆች ወደ አንዱ ቤት በሰ​ን​በት ቀን እህል ሊበላ ገባ፤ እነ​ርሱ ግን ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበር።


ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም አንዱ በእ​ርሱ ዘንድ ምሳ እን​ዲ​በላ ለመ​ነው፤ ወደ ፈሪ​ሳ​ዊ​ውም ቤት ገብቶ በማ​ዕድ ተቀ​መጠ።


ሌዊም በቤቱ ታላቅ ግብዣ አደ​ረ​ገ​ለት፤ ብዙ ሰዎ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ለምሳ ተቀ​ም​ጠው የነ​በሩ ቀራ​ጮ​ችና ኀጢ​አ​ተ​ኞች፥ ሌሎ​ችም ብዙ​ዎች ነበሩ።


ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል?” አሉአቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስና ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።


ይህ​ንም ሲነ​ግ​ራ​ቸው አንድ ፈሪ​ሳዊ በእ​ርሱ ዘንድ ምሳ እን​ዲ​በላ ለመ​ነው፤ ገብ​ቶም ለምሳ ተቀ​መጠ።


የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?


የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘እነሆ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።”


መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ እህል ሳይ​በላ ወይ​ንም ሳይ​ጠጣ መጥቶ ነበ​ርና ጋኔን አለ​በት አላ​ች​ሁት።


ጥበ​ብም ከል​ጆ​ችዋ ሁሉ ጸደ​ቀች።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች