Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 7:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ወይስ ምን ልታዩ ወጥ​ታ​ች​ኋል? ቀጭን ልብስ የለ​በ​ሰ​ውን ሰው ነውን? እነሆ፥ በክ​ብር ልብስ ያጌ​ጡስ በነ​ገ​ሥ​ታት ቤት አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እኮ! ምን ልታዩ ወጣችሁ? ያማረ ልብስ የለበሰውን ሰው ነውን? ባማረ ልብስ የሚሽሞነሞኑና በድሎት የሚኖሩ በቤተ መንግሥት አሉላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ያማረ ልብስ የለበሰውን ሰውን? እነሆ፥ ጌጠኛ ልብስ የሚለብሱና በቅምጥልነት የሚኖሩ በነገሥታት ቤት አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ደግሞስ ምን ለማየት ወጣችሁ? የተዋበ ልብስ የለበሰውን ሰው ለማየት ነውን? የተዋበ ልብስ የሚለብሱና በድሎት የሚኖሩማ በነገሥታት ቤት ይገኛሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ቀጭን ልብስ የለበሰውን ሰውን? እነሆ፥ ጌጠኛ ልብስ የሚለብሱና በቅምጥልነት የሚኖሩ በነገሥታት ቤት አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 7:25
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም።


ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፤ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበረ።


ጽድ​ቅ​ንም እንደ ጥሩር ለበሰ፤ በራ​ሱም ላይ የማ​ዳ​ንን ራስ ቍር አደ​ረገ፤ የበ​ቀ​ል​ንም ልብስ ለበሰ።


እነ​ር​ሱም፥ “ሰው​ዬው ጠጕ​ራም ነው፤ በወ​ገ​ቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር” አሉት። እር​ሱም፥ “ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ ነው” አላ​ቸው።


የሰ​ሎ​ሞ​ን​ንም የማ​ዕ​ዱን መብል፥ የብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም አቀ​ማ​መጥ፥ የሎ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ሥር​ዐት፥ አለ​ባ​በ​ሳ​ቸ​ው​ንም፥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹ​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ባየች ጊዜ ተደ​ነ​ቀች።


ዛሬ የሰ​ማ​ንያ ዓመት ሽማ​ግሌ ነኝ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን መለ​የት እች​ላ​ለ​ሁን? እኔ ባሪ​ያህ የም​በ​ላ​ው​ንና የም​ጠ​ጣ​ውን ጣዕ​ሙን መለ​የት እች​ላ​ለ​ሁን? የወ​ን​ዱ​ንና የሴ​ቲ​ቱን ዘፈን ድምፅ መስ​ማ​ትስ እች​ላ​ለ​ሁን? እኔ ባሪ​ያህ በጌ​ታዬ በን​ጉሡ ላይ ለምን እከ​ብ​ድ​ብ​ሃ​ለሁ?


ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።


የዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከሄዱ በኋላ ለሕ​ዝቡ ስለ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመር፥ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣ​ችሁ? ከነ​ፋስ የተ​ነሣ የሚ​ወ​ዛ​ወዝ ሸን​በ​ቆን ነውን?


ወይስ ምን ልታዩ ወጥ​ታ​ች​ኋል? ነቢ​ይን ነውን? አዎን፥ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከነ​ቢ​ይም ይበ​ል​ጣል።


“አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ቀይ ሐርና ነጭ ሐር፥ እጅ​ግም ቀጭን ልብስ ይለ​ብስ ነበር፤ ዘወ​ት​ርም ተድ​ላና ደስታ ያደ​ርግ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች