Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 7:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ያን​ጊ​ዜም ብዙ​ዎ​ችን ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውና ከሕ​መ​ማ​ቸው ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ን​ትም ፈወ​ሳ​ቸው፤ ለብ​ዙ​ዎች ዕው​ራ​ንም እን​ዲ​ያዩ ብር​ሃ​ንን ሰጣ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በዚያ ጊዜ ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን ከበሽታ፣ ከደዌና ከርኩሳን መናፍስት ፈወሳቸው፤ የብዙ ዐይነ ስውራንንም ዐይን አበራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በዚያች ሰዓት ኢየሱስ ከደዌና ከሚያሠቃይ በሽታ፥ ከክፉዎች መናፍስትም ብዙዎችን ፈወሰ፤ ለብዙ ዐይነ ስውሮችም የማየትን ጸጋ ሰጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ኢየሱስ በዚያኑ ሰዓት ሰዎችን ከልዩ ልዩ በሽታና ደዌ ፈወሰ፤ ርኩሳን መናፍስትንም አስወጣ፤ የብዙ ዕውሮችን ዐይን አበራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በዚያች ሰዓት ከደዌና ከሥቃይ ከክፉዎች መናፍስትም ብዙዎችን ፈወሰ፥ ለብዙ ዕውሮችም ማየትን ሰጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 7:21
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ብዙ ሰዎችን አድኖ ነበርና፥ ስለዚህም ሥቃይ ያለባቸው ሁሉ እንዲዳስሱት ይወድቁበት ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ደ​ውን ይገ​ሥ​ጻ​ልና፥ የሚ​ወ​ደ​ደ​ው​ንም ልጅ ሁሉ ይገ​ር​ፈ​ዋል” ብሎ የሚ​ነ​ጋ​ገ​ረ​ውን ምክር ረስ​ታ​ች​ኋል።


እርሱም “ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፤ ከሥቃይሽም ተፈወሽ፤” አላት።


ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ፤ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች።


ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።


“በም​ድር ላይም ራብ፥ ወይም ቸነ​ፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረ​ማሞ ቢሆን፥ አን​በጣ፥ ወይም ኩብ​ኩባ ቢመጣ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህም ጠላት ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው በአ​ን​ዲቱ ከብቦ ቢያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥


ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ እርሱ ደር​ሰው፥ “የሚ​መ​ጣው አንተ ነህን? ወይስ ተስፋ የም​ና​ደ​ር​ገው ሌላ አለ? ብሎ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ወደ አንተ ልኮ​ናል” አሉት።


“ካህ​ኑም ገብቶ ቢያ​የው፥ እነ​ሆም፥ ቤቱ ከተ​መ​ረገ በኋላ ደዌው በቤቱ ውስጥ ባይ​ሰፋ፥ ደዌው ስለ ሻረ ካህኑ ቤቱን፦ ንጹሕ ነው ይለ​ዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች