Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 6:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ለሚ​ለ​ም​ን​ህም ሁሉ ስጥ፤ ገን​ዘ​ብ​ህን የሚ​ወ​ስ​ደ​ው​ንም እን​ዲ​መ​ልስ አት​ጠ​ይ​ቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፤ ንብረትህን የሚወስድ እንዲመልስልህ አትጠይቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፤ ንብረትህንም የሚወስድብህን ሰው እንዲመልስ አትጠይቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፤ ንብረትህን የሚወስድብህን ሰው እንዲመልስ አትጠይቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፥ ገንዘብህንም የሚወስድ እንዲመልስ አትጠይቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 6:30
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ቸር​ነ​ቱን ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ርሱ ድህ​ነት እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለ​ጸጋ ሲሆን፥ ስለ እና​ንተ ራሱን ድሃ አደ​ረገ።


በድ​ካ​ማ​ች​ንና በሥ​ራ​ችን ነዳ​ያ​ንን እን​ቀ​በ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ደ​ሚ​ገ​ባን ይህን አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ‘ከሚ​ቀ​በል ይልቅ የሚ​ሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለ​ው​ንም የጌ​ታ​ች​ንን የኢ​የ​ሱ​ስን ቃል ዐስቡ።”


እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ሰምቶ እን​ዲህ አለው፥ “አን​ዲት ቀር​ታ​ሃ​ለች፤ ሂድና ያለ​ህን ሁሉ ሸጠህ ለነ​ዳ​ያን ስጥ፤ በሰ​ማ​ይም መዝ​ገብ ታገ​ኛ​ለህ፤ መጥ​ተ​ህም ተከ​ተ​ለኝ።”


ኃጥእ ቀኑን ሁሉ ክፉ ምኞትን ይመኛል፥ ጻድቅ ግን ዐውቆ ይራራል፥ ይመጸውታልም።


ዋሊያ ወደ ውኃ ምን​ጮች እን​ደ​ሚ​ና​ፍቅ፥ እን​ዲሁ ነፍሴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትና​ፍ​ቃ​ለች።


ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ እንደ ስጦታውም መልሶ ይከፍለዋል።


ሀብ​ታ​ች​ሁን ሸጣ​ችሁ ምጽ​ዋት ስጡ፤ ሌባ በማ​ያ​ገ​ኝ​በት ነቀ​ዝም በማ​ያ​በ​ላ​ሽ​በት፥ የማ​ያ​ረጅ ከረ​ጢት፥ የማ​ያ​ል​ቅም መዝ​ገብ በሰ​ማ​ያት ለእ​ና​ንተ አድ​ርጉ።


ነገር ግን የሚ​ወ​ደ​ደ​ውን ምጽ​ዋት አድ​ር​ጋ​ችሁ ስጡ፤ ሁሉም ንጹሕ ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል።


ስጡ፥ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልም፤ የሞ​ላና የበዛ፥ የተ​ት​ረ​ፈ​ረ​ፈም መል​ካም መስ​ፈ​ሪያ በዕ​ቅ​ፋ​ችሁ ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ በሰ​ፈ​ራ​ች​ሁ​በ​ትም መስ​ፈ​ሪያ ይሰ​ፍ​ሩ​ላ​ች​ኋል።”


ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።”


ጥበ​ብን አውቅ ዘንድ በም​ድር የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም ድካም አይ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ በቀ​ንና በሌ​ሊት እን​ቅ​ል​ፍን በዐ​ይኑ የሚ​ያይ የለ​ምና።


ለድሃ የሚራራ እርሱ ይበላል እንጀራውን ለድሃ ሰጥቶአልና። ለሰጠው ሀብታምም የሚከፍል አይደለምና። መማለጃን የሰጠ ሰው ድል መንሣትንና ሞገስን ያገኛል፥ ነገር ግን የተቀበለውን ነፍስ ያጠፋል።


መካ​ኒ​ቱን በቤቱ የሚ​ያ​ኖ​ራት፥ ደስ የተ​ሰ​ኘ​ችም የል​ጆች እናት የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት።


የሚ​ሰ​ር​ቅም እን​ግ​ዲህ አይ​ስ​ረቅ፤ ነገር ግን ድሃ​ውን ይረዳ ዘንድ በእ​ጆቹ መል​ካም እየ​ሠራ ይድ​ከም።


ለሰ​ባት፥ ደግ​ሞም ለስ​ም​ን​ት​ዕ​ድል ፈን​ታን ስጥ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ሆ​ነ​ውን ክፉ ነገር ምን እንደ ሆነ አታ​ው​ቅ​ምና።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤


ጕን​ጭ​ህን ለሚ​መ​ታ​ህም ሁለ​ተ​ኛ​ይ​ቱን ስጠው፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ህን ለሚ​ወ​ስ​ድም ቀሚ​ስ​ህን ደግሞ አት​ከ​ል​ክ​ለው።


ሰዎች ሊያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​ወ​ዱ​ትም እን​ዲሁ እና​ንተ አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች