Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በዚ​ያም ወራት ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊ​ቱን ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልይ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከእነዚያም ቀናት በአንዱ ኢየሱስም ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጥቶ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ዐደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በነዚህም ወራት ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊቱንም በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አንድ ቀን ኢየሱስ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ፤ እዚያ ሌሊቱን ሙሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ዐደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 6:12
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በለ​መ​ለመ መስክ ያሳ​ድ​ረ​ኛል፤ በዕ​ረ​ፍት ውኃ ዘንድ አሳ​ደ​ገኝ።


አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ትእ​ዛ​ዝህ በም​ድር ላይ ብር​ሃን ነውና ነፍሴ በሌ​ሊት ወደ አንተ ትገ​ሠ​ግ​ሣ​ለች። በም​ድር የም​ት​ኖ​ሩም ጽድቅ መሥ​ራ​ትን ተማሩ።


ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤


አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።


ማለዳም ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ፤ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ።


ወደ ተራራም ወጣ፤ ራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ፤ ወደ እርሱም ሄዱ።


ካሰናበታቸውም በኋላ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።


እርሱ ግን ወደ ምድረ በዳ እየ​ወጣ ይጸ​ልይ ነበር።


እነ​ርሱ ግን፥ እጅግ ተቈጡ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱ​ስም ምን እን​ድ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​በት እርስ በር​ሳ​ቸው ተማ​ከሩ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወርዶ በሰፊ ቦታ ቆመ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወገን ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከመ​ላው ይሁ​ዳና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ከጢ​ሮ​ስና ከሲ​ዶና ባሕር ዳርቻ ትም​ህ​ር​ቱን ሊሰሙ፥ ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውም ሊፈ​ወሱ የመ​ጡት ከሕ​ዝቡ ወገን እጅግ ብዙ​ዎች ነበሩ።


ከዚ​ህም በኋላ ብቻ​ውን ሲጸ​ልይ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ሳሉ፥ “ሰዎች ማን ይሉ​ኛል?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው።


ከዚ​ህም ነገር በኋላ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ጴጥ​ሮ​ስን፥ ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዮሐ​ን​ስን ይዞ​አ​ቸው ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ።


ሲጸ​ል​ይም የፊቱ መልክ ተለ​ወጠ፤ ልብ​ሱም ነጭ ሆነ፤ እንደ መብ​ረ​ቅም አብ​ለ​ጨ​ለጨ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ተራራ ወጣ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ጋር በዚያ ተቀ​መጠ።


በም​ስ​ጋና እየ​ተ​ጋ​ችሁ ለጸ​ሎት ፅሙ​ዳን ሁኑ።


እር​ሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ፥ በታ​ላቅ ጩኸ​ትና እንባ ከሞት ሊያ​ድ​ነው ወደ​ሚ​ች​ለው ጸሎ​ት​ንና ምል​ጃን አቀ​ረበ፤ ጽድ​ቁ​ንም ሰማው።


“ሳኦል እኔን ከመ​ከ​ተል ተመ​ል​ሶ​አ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም አል​ፈ​ጸ​መ​ምና ስላ​ነ​ገ​ሥ​ሁት ተጸ​ጸ​ትሁ።” ሳሙ​ኤ​ልም አዘነ። ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች