ሉቃስ 5:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ትምህርቱንም ከፈጸመ በኋላ ስምዖንን፥ “ወደ ጥልቁ ባሕር ፈቀቅ በል፤ መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ስምዖንን፣ “ወደ ጥልቁ ውሃ ፈቀቅ በልና ዓሣ ለመያዝ መረባችሁን ጣሉ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ንግግሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ “ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል፤ መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ፤” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ንግግሩንም ከጨረሰ በኋላ ስምዖንን፦ “ጀልባዋን ወደ ጥልቁ ባሕር ራቅ አድርገህ አንተና ጓደኞችህ ዓሣ ለማጥመድ መረባችሁን ጣሉ፤” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ነገሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን፦ ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ አለው። ምዕራፉን ተመልከት |