Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 5:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 አዲስ ጠጅ​ንም በአ​ሮጌ ረዋት የሚ​ያ​ደ​ርግ የለም፤ ያለ​ዚያ ግን ይቀ​ድ​ደ​ዋል፤ ወይ​ኑም ይፈ​ስ​ሳል፤ ረዋ​ቱም ይቀ​ደ​ዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 አዲስ የወይን ጠጅም በአሮጌ አቍማዳ ጨምሮ የሚያስቀምጥ ማንም የለም፤ እንዲህ ቢያደርግ አዲሱ የወይን ጠጅ አቍማዳውን ያፈነዳዋል፤ የወይን ጠጁም ይፈስሳል፤ አቍማዳውም ከጥቅም ውጭ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ባረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር ማንም የለም፤ ቢደረግ ግን አዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፤ እርሱም ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከጥቅም ውጪ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 እንዲሁም በአረጀ የወይን ጠጅ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር ማንም የለም፤ ቢደረግ ግን አዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፤ የወይን ጠጁም ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከጥቅም ውጪ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ባረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳል፥ እርሱም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 5:37
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፤ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።”


በም​ሳ​ሌም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በአ​ሮጌ ልብስ ቀዳዳ ላይ የአ​ዲስ ልብስ እራፊ የሚ​ጥፍ የለም፤ ያለ​ዚያ ግን አዲሱ አሮ​ጌ​ውን ይቀ​ድ​ደ​ዋል፤ አዲሱ እራ​ፊም ከአ​ሮ​ጌው ጋር አይ​ስ​ማ​ማም።


ነገር ግን አዲ​ሱን ጠጅ በአ​ዲስ ረዋት ያደ​ር​ጉ​ታል፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ይጠ​ባ​በ​ቃሉ።


እነ​ዚ​ህም የጠጅ ረዋ​ቶች አዲ​ሶች ሳሉ ሞላ​ን​ባ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ አር​ጅ​ተው ተቀ​ድ​ደ​ዋል፤ መን​ገ​ዳ​ች​ንም እጅግ ስለ ራቀ​ብን እነ​ዚህ ልብ​ሶ​ቻ​ች​ንና ጫማ​ዎ​ቻ​ችን አር​ጅ​ተ​ዋል።”


እነ​ርሱ ደግሞ ተን​ኰል አድ​ር​ገው መጡ፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም ስንቅ ያዙ፤ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም ላይ አሮጌ ዓይ​በ​ትና ያረ​ጀና የተ​ቀ​ደደ የተ​ጠ​ቀ​መም የጠጅ ረዋት ተሸ​ከሙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች