Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 5:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሙ​ሽ​ራው ሚዜ​ዎች ሙሽ​ራው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሳለ መጾም አይ​ች​ሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ሙሽራው ዐብሯቸው እያለ ዕድምተኞቹ እንዲጾሙ ማድረግ ይቻላልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎችን ልታጾሙ አትችሉም፤ ትችላላችሁን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እያለ ሚዜዎች መጾም ይገባቸዋል ብላችሁ ታስባላችሁን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ኢየሱስም፦ ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎችን ልታስጦሙ ትችላላችሁን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 5:34
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሙሽራ ያለ​ችው ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚ​ሰ​ማው የሙ​ሽ​ራው ሚዜ ግን በሙ​ሽ​ራው ቃል እጅግ ደስ ይለ​ዋል፤ የእኔ ደስታ አሁን ተፈ​ጸ​መች።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገባ ቅን​ዐት እቀ​ና​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁና፤ ወደ እርሱ አቀ​ር​ባ​ችሁ ዘንድ ለአ​ንዱ ንጹሕ ድን​ግል ሙሽራ ለክ​ር​ስ​ቶስ አጭ​ቻ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


“መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች።


አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።


ጐል​ማ​ሳም ከድ​ን​ግ​ሊቱ ጋር እን​ደ​ሚ​ኖር፥ እን​ዲሁ ልጆ​ችሽ ከአ​ንቺ ጋር ይኖ​ራሉ፤ ሙሽ​ራም በሙ​ሽ​ራ​ዪቱ ደስ እን​ደ​ሚ​ለው፥ እን​ዲሁ አም​ላ​ክሽ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ዋል።


ፈጣ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ታዳ​ጊሽ ነው፤ እር​ሱም በም​ድር ሁሉ እን​ደ​ዚሁ ይጠ​ራል።


አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ከአ​ንቺ ጋር እን​ፈ​ል​ገው ዘንድ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ወዴት ሄደ? ልጅ ወን​ድ​ም​ሽስ ወዴት ፈቀቅ አለ?


እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ በም​ድረ በዳ ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ልጅ ወን​ድ​ሜን ያገ​ኛ​ች​ሁት እንደ ሆነ፥ እኔ ከፍ​ቅር የተ​ነሣ መታ​መ​ሜን ትነ​ግ​ሩት ዘንድ።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።


እነ​ር​ሱም፥ “የዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ስለ​ምን በብዙ ይጾ​ማሉ? ጸሎ​ትስ ስለ​ምን ያደ​ር​ጋሉ? የፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገ​ኖች የሆ​ኑ​ትም ስለ​ምን እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ? ያንተ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ግን ለምን ይበ​ላሉ? ይጠ​ጣ​ሉም?” አሉት።


ነገር ግን ሙሽ​ራ​ውን ከእ​ነ​ርሱ የሚ​ወ​ስ​ዱ​በት ቀን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊ​ዜም ይጾ​ማሉ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች