Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 5:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እነ​ር​ሱም፥ “የዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ስለ​ምን በብዙ ይጾ​ማሉ? ጸሎ​ትስ ስለ​ምን ያደ​ር​ጋሉ? የፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገ​ኖች የሆ​ኑ​ትም ስለ​ምን እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ? ያንተ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ግን ለምን ይበ​ላሉ? ይጠ​ጣ​ሉም?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እነርሱም፣ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አብዛኛውን ጊዜ ይጾማሉ፤ ይጸልያሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንደዚሁ ያደርጋሉ፤ የአንተዎቹ ግን ይበላሉ፤ ይጠጣሉ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አዘውትረው ይጾማሉ፤ ጸሎትም ያደርሳሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ ይጠጣሉም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስን፦ “የዮሐንስና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት ብዙ ጊዜ ይጾማሉ፤ ይጸልያሉም፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ሁልጊዜ የሚበሉትና የሚጠጡት ለምንድን ነው?” በማለት ጠየቁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 እነርሱም፦ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለ ምን ብዙ ይጦማሉ ጸሎትስ ስለ ምን ያደርጋሉ፥ ደግሞም የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት ስለ ምን እንደዚሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ ይጠጣሉም? አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 5:33
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የመ​በ​ለ​ቶ​ችን ገን​ዘብ የሚ​በሉ፥ ለም​ክ​ን​ያት ጸሎ​ት​ንም የሚ​ያ​ስ​ረ​ዝሙ እነ​ዚህ ታላቅ ፍር​ድን ይቀ​በ​ላሉ።”


እኔ በየ​ሳ​ም​ንቱ ሁለት ቀን እጾ​ማ​ለሁ፤ ከማ​ገ​ኘ​ውም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ እሰ​ጣ​ለሁ።’


ጌታም፥ “ተነ​ሣና ቅን በም​ት​ባ​ለው መን​ገድ ሂድ፤ በይ​ሁዳ ቤትም ከጠ​ር​ሴስ ሀገር የመጣ ሳውል የሚ​ባል ሰው ፈልግ፤ እርሱ አሁን ይጸ​ል​ያ​ልና” አለው።


ከዚ​ህም በኋላ በዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትና በአ​ይ​ሁድ መካ​ከል ስለ ማን​ጻት ክር​ክር ሆነ፤


በማ​ግ​ሥ​ቱም ደግሞ ዮሐ​ንስ ከሁ​ለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ቆሞ ሳለ፥


ከዚ​ህም በኋላ በአ​ን​ዲት ቦታ ጸለየ፤ ጸሎ​ቱን በጨ​ረሰ ጊዜም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ፥ ዮሐ​ንስ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እንደ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው ጸሎት አስ​ተ​ም​ረን” አለው።


የመበለቶችን ቤት የሚበሉ፤ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።”


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


በምትበሉበትና በምትጠጡበትስ ጊዜ፥ ለራሳችሁ የምትበሉና የምትጠጡ አይደላችሁምን?


እጃ​ች​ሁን ወደ እኔ ብት​ዘ​ረጉ፥ ዐይ​ኖ​ችን ከእ​ና​ንተ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምህ​ላ​ንም ብታ​በዙ አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጆ​ቻ​ችሁ ደምን ተሞ​ል​ተ​ዋ​ልና።


ሰማ​ንያ አራት ዓመ​ትም መበ​ለት ሆና ኖረች፤ በጾ​ምና በጸ​ሎ​ትም እያ​ገ​ለ​ገ​ለች፥ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቤተ መቅ​ደስ አት​ወ​ጣም ነበር።


ኃጥ​ኣ​ንን ወደ ንስሓ እንጂ ጻድ​ቃ​ንን ልጠራ አል​መ​ጣ​ሁም።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሙ​ሽ​ራው ሚዜ​ዎች ሙሽ​ራው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሳለ መጾም አይ​ች​ሉም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች