Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 5:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ለሰው ልጅ በም​ድር ላይ ኀጢ​አ​ትን ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለው እን​ድ​ታ​ውቁ፤ ያን ሽባ፦ ተነ​ሣና አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ወደ ቤትህ ሂድ ብዬ​ሃ​ለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ነገር ግን ይህን ያልሁት የሰው ልጅ በምድር ላይ ኀጢአትን ለማስተስረይ ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ ነው።” ከዚያም ሽባውን ሰው፣ “ተነሥተህ ዐልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ እልሃለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን የማስተስረይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤” ብሎ፥ መንቀሳቅስ የተሳነውን ሰው፦ “እነሆ አዝሃለሁ፤ ተነሣ፤ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ለመደምሰስ ሥልጣን እንዳለው ማወቅ አለባችሁ” ብሎ ሽባውን ሰው፦ “አንተ ሰው ተነሥ፤ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ!” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአት ሊያስተሰርይ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ ብሎ፥ ሽባውን፦ አንተን እልሃለሁ፥ ነተሣ፥ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 5:24
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰ ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ው​ነቱ ሕማ​ምን ያርቅ ዘንድ ይወ​ዳል፤ ብር​ሃ​ን​ንም ያሳ​የ​ዋል፤ በጥ​በ​ቡም ይለ​የ​ዋል፤ ለጽ​ድ​ቅና ለበጎ ነገር የሚ​ገ​ዛ​ውን ጻድ​ቁን ያጸ​ድ​ቀ​ዋል። የብ​ዙ​ዎ​ች​ንም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን እርሱ ይደ​መ​ስ​ሳል።


ድም​ፁ​ንም ከፍ አድ​ርጎ፥ “ተነ​ሥና ቀጥ ብለህ በእ​ግ​ርህ ቁም እል​ሃ​ለሁ” አለው፤ ወዲ​ያ​ው​ኑም ተነ​ሥቶ ተመ​ላ​ለሰ።


ጴጥ​ሮ​ስም ሁሉን ካስ​ወጣ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ ጸለየ፤ ወደ በድ​ን​ዋም መለስ ብሎ፥ “ጣቢታ ሆይ፥ ተነሽ” አላት፤ እር​ስ​ዋም ዐይ​ኖ​ች​ዋን ገለ​ጠች፤ ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮ​ስን አየ​ችው፤ ቀና ብላም ተቀ​መ​ጠች።


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ኤንያ ሆይ፥ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ይፈ​ው​ስህ፤ ተነ​ሥና አል​ጋ​ህን አን​ጥፍ” አለው፤ ያን​ጊ​ዜም ተነሣ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ሱን ለእ​ስ​ራ​ኤል ንስ​ሓን፥ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ስር​የት ይሰጥ ዘንድ ራስም አዳ​ኝም አደ​ረ​ገው፤ በቀ​ኙም አስ​ቀ​መ​ጠው።


ሥጋ በለ​በ​ሰው ሁሉ ላይ ሥል​ጣ​ንን እንደ ሰጠ​ኸው መጠን ለሰ​ጠ​ኸው ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ።


ይህ​ንም ብሎ በታ​ላቅ ቃል ጮኸና፥ “አል​ዓ​ዛር፥ ና፤ ወደ ውጭ ውጣ” አለ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ የሰው ልጅ ነውና ይፈ​ርድ ዘንድ ሥል​ጣ​ንን ሰጠው።


ከሰ​ማይ ከወ​ረ​ደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤ እር​ሱም በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው ነው።


እርሱ ግን ሁሉን ወደ ውጭ አስ​ወ​ጣና እጅ​ዋን ይዞ ጠራት፤ እን​ዲ​ህም አላት፥ “ አንቺ ብላ​ቴና ተነሺ።”


ቀር​ቦም ቃሬ​ዛ​ውን ያዘ፤ የተ​ሸ​ከ​ሙ​ትም ቆሙ፤ እር​ሱም፥ “አንተ ጐበዝ ተነሥ እል​ሃ​ለሁ” አለው።


እጁ​ንም ዘር​ግቶ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “እወ​ዳ​ለሁ ንጻ” አለው፤ ያን​ጊ​ዜም ለምጹ ለቀ​ቀው።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።


ኢየሱስም “አንተ አልህ፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ፤” አለው።


“የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤


ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” ብሎ ጠየቀ።


ነገር ግን በምድር ላይ ኀጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤” በዚያን ጊዜ ሽባውን “ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ፤” አለው።


ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


እነሆ፥ ሰዎች በአ​ልጋ ተሸ​ክ​መው ሽባ የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፤ እን​ዲ​ፈ​ው​ሰ​ውም ወደ እርሱ ሊያ​ስ​ገ​ቡት ወደዱ።


ኀጢ​አ​ትህ ተሰ​ረ​የ​ልህ ከማ​ለ​ትና ተነ​ሥ​ተህ ሂድ ከማ​ለት ማና​ቸው ይቀ​ላል?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች