Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 5:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ለማ​ንም እን​ዳ​ይ​ና​ገር ከለ​ከ​ለው፤ “ነገር ግን ሄደህ ራስ​ህን ለካ​ህን አስ​መ​ር​ምር፤ ምስ​ክ​ርም ይሆ​ን​ባ​ቸው ዘንድ ስለ ነጻህ ሙሴ እንደ አዘዘ መባ​ህን አቅ​ርብ” ብሎ አዘ​ዘው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ኢየሱስም፣ “ይህን ለማንም አትናገር፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱ ምስክር እንዲሆንም ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ” ሲል አዘዘው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እርሱም ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፤ ነገር ግን፦ “ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ይህን ነገር ለማንም አትናገር፤ ነገር ግን በቀጥታ ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለሕዝብ ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እርሱም ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፥ ነገር ግን፦ ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፥ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 5:14
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባያ​ቸ​ውም ጊዜ፥ “ወደ ካህን ሂዱና ራሳ​ች​ሁን አስ​መ​ር​ምሩ” አላ​ቸው፤ ሲሄ​ዱም ነጹ።


ኢየሱስም “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ” አለው።


“ለማንም አንዳች እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን አቅርብ፤” አለው።


በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል


ዐይኖቻቸውም ተከፈቱ። ኢየሱስም “ማንም እንዳያውቅ ተጠንቀቁ፤” ብሎ በብርቱ አዘዛቸው።


“ሰው በሥ​ጋው ቆዳ ላይ እባጭ ብት​ወ​ጣ​በት፥ ብት​ነ​ጣም፥ በሥ​ጋ​ውም ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ብት​መ​ስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካ​ህ​ናቱ ልጆች ወደ አንዱ ያም​ጡት።


የማ​ይ​ቀ​በ​ሉ​አ​ችሁ ቢሆን ግን ከዚ​ያች ከተማ ወጥ​ታ​ችሁ ምስ​ክር ሊሆ​ን​ባ​ቸው የእ​ግ​ራ​ች​ሁን ትቢያ አራ​ግፉ።”


ከማይቀበሉአችሁና ከማይሰሙአችሁ ስፍራ ሁሉ፥ ከዚያ ወጥታችሁ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ ከእግራችሁ በታች ያለውን ትቢያ አራግፉ። እውነት እላችኋለሁ፤ ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ በፍርድ ቀን ይቀልላቸዋል፤” አላቸው።


ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ።


ደዌው በል​ብሱ ወይም በቆ​ዳው ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በሚ​ደ​ረ​ገው ነገር አረ​ን​ጓዴ ወይም ቀይ ቢሆን፥ የለ​ምጽ ደዌ ነው፤ ለካ​ህኑ ያሳ​ያል።


እጁ​ንም ዘር​ግቶ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “እወ​ዳ​ለሁ ንጻ” አለው፤ ያን​ጊ​ዜም ለምጹ ለቀ​ቀው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች