Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 4:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ስለ​ዚህ አንተ በፊቴ ብት​ሰ​ግ​ድ​ልኝ ይህ ሁሉ ለአ​ንተ ይሁ​ን​ልህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህ ብትሰግድልኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስለዚህ አንተ ለእኔ ብትሰግድልኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናል አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 4:7
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ባየው ጊዜ ጮኸ፤ ሮጦም ሰገ​ደ​ለት፤ “የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር ምን አለኝ?” እያ​ለም በታ​ላቅ ቃል ጮኸ፤ እን​ዳ​ያ​ሠ​ቃ​የ​ውም ማለ​ደው።


ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።


መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።


ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ “ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኀይልም ልትቀበል ይገባሃል፤” ክብር ውዳሴ ኃይልም እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።


በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ሰው​የ​ውም ሳም​ራዊ ነበር።


ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።


ወር​ቁ​ንና ብሩን ከኮ​ሮጆ የሚ​ያ​ወ​ጡና በሚ​ዛን የሚ​መ​ዝኑ እነ​ርሱ አን​ጥ​ረ​ኛ​ውን ይቀ​ጥ​ራሉ፤ እር​ሱም ጣዖት አድ​ርጎ ይሠ​ራ​ዋል፤ ለዚ​ያም ይጐ​ነ​በ​ሱ​ለ​ታል፤ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ት​ማል።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ግብ​ፅና የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥ​ሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም ይገ​ዙ​ል​ሃል፤ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ታስ​ረው በኋ​ላህ ይከ​ተ​ሉ​ሃል፤ በፊ​ት​ህም ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም እየ​ሰ​ገዱ፦ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ የለም ብለው ይለ​ም​ኑ​ሃል።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዴት ያው​ቃል? በአ​ር​ያ​ምስ በውኑ የሚ​ያ​ውቅ አለን?” ይላሉ።


ዲያ​ብ​ሎ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ይህን ሁሉ ግዛት፥ ይህ​ንም ክብር ለአ​ንተ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ለእኔ ተሰ​ጥ​ቶ​አ​ልና፤ ለወ​ደ​ድ​ሁ​ትም እሰ​ጠ​ዋ​ለ​ሁና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ሰይ​ጣን ከኋ​ላዬ ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ክህ ልት​ሰ​ግድ፥ እር​ሱ​ንም ብቻ ልታ​መ​ልክ ተጽ​ፎ​አል” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች