ሉቃስ 4:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)38 ከምኵራቡም ወጥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ፤ የስምዖን አማትም በብርቱ ንዳድ ታማ ነበርና ስለ እርስዋ ነገሩት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም38 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከምኵራብ ወጥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም ዐማት ኀይለኛ ትኵሳት ይዟት ታምማ ነበር፤ እንዲፈውሳትም ስለ እርሷ ለመኑት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)38 ከምኵራብም ተነሥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት በብርቱ ትኩሳት ታማ ነበር፤ ስለ እርሷም ለመኑት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም38 ኢየሱስ ከምኲራብ ተነሥቶ ወደ ስምዖን ቤት ሄደ፤ እዚያም የስምዖን ዐማት በጣም አተኲሶአት ታማ ተኝታ ነበር፤ ስለዚህ እንዲያድናት ኢየሱስን ለመኑት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)38 በምኵራብም ተነሥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት በብርቱ ንዳድ ታማ ነበር ስለ እርስዋም ለመኑት። ምዕራፉን ተመልከት |