Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 4:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሁሉም የን​ግ​ግ​ሩን መከ​ና​ወን መሰ​ከ​ሩ​ለት፤ የአ​ን​ደ​በ​ቱ​ንም ቅል​ጥ​ፍና እያ​ደ​ነቁ፥ “ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ አይ​ደ​ለ​ምን?” ይሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሁሉም ስለ እርሱ በበጎ ይናገሩ ነበር፤ ደግሞም ከአንደበቱ በሚወጣ የጸጋ ቃል እየተገረሙ፣ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር፤ ከአፉም ከሚወጡት ቃላት ጸጋ የተነሣ እየተደነቁ፦ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ስለ እርሱ ሁሉም መልካም ይናገሩ ነበር፤ በሚናገረውም ጸጋን የተመላ ቃል ተደንቀው “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር ከአፉም ከሚወጣው ከጸጋው ቃል የተነሣ እየተደነቁ፦ ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን? ይሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 4:22
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ​ዚህ ምድር ብት​ነ​ዋ​ወጥ፥ ተራ​ሮ​ችም ወደ ባሕር ልብ ቢፈ​ልሱ አን​ፈ​ራም።


ፈሳሽ ወንዝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከተማ ደስ ያሰ​ኛል፤ ልዑል ማደ​ሪ​ያ​ውን ቀደሰ።


የጻድቃን ከንፈሮች ሞገስን ያፈስሳሉ፤ የኃጥኣን አፍ ግን ከዕውቀት ይከለከላል።


ጠቢብን ሰዎች ዐዋቂ ይሉታል፥ ነገሩም ጣፋጭ የሆነውን እጅግ ያደምጡታል።


የጠ​ቢብ ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት፤ የሰ​ነፍ ከን​ፈ​ሮች ግን ራሱን ይው​ጡ​ታል።


ጕሮ​ሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለ​ን​ተ​ና​ውም የተ​ወ​ደደ ነው፤ እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ልጅ ወን​ድሜ ይህ ነው፥ ወዳ​ጄም ይህ ነው።


የም​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በብ ምላ​ስን ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነ​ቃ​ኛል፤ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮን ሰጥ​ቶ​ኛል።


የሰ​ሙ​ትም ሁሉ አስ​ተ​ዋ​ይ​ነ​ቱ​ንና አመ​ላ​ለ​ሱን ያደ​ንቁ ነበር።


በአ​ዩ​ትም ጊዜ ደነ​ገጡ፤ እና​ቱም፥ “ልጄ፥ ለምን እን​ዲህ አደ​ረ​ግ​ኸን? እነሆ አባ​ት​ህም፥ እኔም ስን​ፈ​ል​ግህ ደከ​ምን” አለ​ችው።


በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነሡ ሊመ​ል​ሱ​ላ​ች​ሁና ሊከ​ራ​ከ​ሯ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ችሉ እኔ አፍ​ንና ጥበ​ብን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


እር​ሱም፥ “የዚህ የመ​ጽ​ሐፍ ነገር ዛሬ በጆ​ሮ​አ​ችሁ ደረሰ፤ ተፈ​ጸ​መም” ይላ​ቸው ጀመር።


ፊል​ጶስ ግን ከእ​ን​ድ​ር​ያ​ስና ከጴ​ጥ​ሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበር።


“እኛ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን የም​ና​ው​ቃ​ቸው ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ ኢየ​ሱስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ግ​ዲህ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወረ​ድሁ ይለ​ናል?” አሉ።


ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም መል​ሰው፥ “ያ ሰው እንደ ተና​ገ​ረው ያለ ከቶ ሰው አል​ተ​ና​ገ​ረም” አሉ​አ​ቸው።


ነገር ግን ይቃ​ወ​ሙት ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ በጥ​በ​ብና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበ​ርና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች