Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ዮሐ​ን​ስም የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ሄሮ​ድ​ስን የወ​ን​ድ​ሙን የፊ​ል​ጶ​ስን ሚስት ሄሮ​ድ​ያ​ዳን ስለ​ማ​ግ​ባ​ቱና ሄሮ​ድስ ያደ​ር​ገው ስለ​ነ​በ​ረው ክፉ ነገር ሁሉ ይገ​ሥ​ጸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ነገር ግን ዮሐንስ፣ የአራተኛውን ክፍል ገዥ ሄሮድስን የወንድሙ ሚስት በነበረችው በሄሮድያዳ ምክንያትና ስለ ሌሎች ሥራዎቹ በገሠጸው ጊዜ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 አገረ ገዥ ሄሮድስ ግን፥ ስለ ወንድሙ ሚስት ስለ ሄሮድያዳና ሄሮድስ ስላደረገው ክፋት ሁሉ በዮሐንስ ስለ ተገሠጸ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የገሊላውን ገዢ ሄሮድስን ግን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን በማግባቱና ሌላም ብዙ ክፉ ነገር በማድረጉ ገሠጸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ ግን፥ ስለ ሄሮድያዳ ስለ ወንድሙ ስለ ፊልጶስ ሚስትና ሄሮድስ ስላደረገው ሌላ ክፋት ሁሉ ዮሐንስ ስለ ገሠጸው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 3:19
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አላዋቂ ሰው የሚዘልፈውን አይወድድም፥ ከጠቢባንም ጋር አይነጋገርም።


ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና


በዚያ ዘመን የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ የኢየሱስን ዝና ሰማ፤


ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች፤ ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤


ጢባ​ር​ዮስ ቄሣር በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አም​ስት ዓመት ጴን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ የይ​ሁዳ ገዢ ሆኖ ሳለ፥ ሄሮ​ድ​ስም በገ​ሊላ የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ሳለ፥ ወን​ድሙ ፊል​ጶ​ስም የኢ​ጡ​ር​ያ​ስና የጥ​ራ​ኮ​ኒ​ዶስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ፥ ሊሳ​ን​ዮ​ስም የሳ​ብ​ላ​ኒስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ ሆነው ሳሉ፥


ሕዝ​ቡ​ንም ይገ​ስ​ጻ​ቸ​ውና በሌ​ላም በብዙ ነገር የም​ሥ​ራች ይነ​ግ​ራ​ቸው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች