Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 24:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ከዚ​ህም በኋላ አብ​ሮ​አ​ቸው ለማ​ዕድ ተቀ​ምጦ ሳለ እን​ጀ​ራ​ውን አን​ሥቶ ባረከ፤ ቈር​ሶም ሰጣ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ዐብሯቸውም በማእድ በተቀመጠ ጊዜ፣ እንጀራውን አንሥቶ ባረከ፤ ቈርሶም ሰጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ከእነርሱም ጋር በማዕድ በተቀመጠ ጊዜ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፤ ቈርሶም ሰጣቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ከእነርሱም ጋር በማእድ ተቀመጠ፤ እንጀራ አንሥቶ የምስጋና ጸሎት ካደረገ በኋላ ቈርሶ ሰጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 24:30
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝቡም በሣር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፤ እንጀራውንም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ።


እነ​ር​ሱም በመ​ን​ገድ የሆ​ነ​ው​ንና እን​ጀ​ራ​ውን ሲቈ​ርስ ጌታ​ች​ንን እን​ዴት እን​ዳ​ወ​ቁት ነገ​ሩ​አ​ቸው።


አም​ስ​ቱን እን​ጀ​ራና ሁለ​ቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ተመ​ለ​ከተ፤ ባረከ፤ ቈር​ሶም ለሕ​ዝቡ እን​ዲ​ያ​ቀ​ርቡ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሰጣ​ቸው።


ሰባቱንም እንጀራ ዓሣውንም ይዞ አመሰገነ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ።


ይህ​ንም ተና​ግሮ ኅብ​ስ​ቱን አን​ሥቶ በሁ​ሉም ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ ቈር​ሶም ይበላ ዘንድ ጀመረ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን እን​ጀራ ይዞ አመ​ሰ​ገነ፤ ቈር​ሶም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሰጣ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ለተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች ሰጡ​አ​ቸው፤ ከዓ​ሣ​ውም እን​ዲሁ የፈ​ለ​ጉ​ትን ያህል ሰጡ​አ​ቸው።


ኅብ​ስ​ቱ​ንም አነሣ፤ አመ​ስ​ገነ፤ ፈት​ቶም ሰጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ስለ እና​ንተ ቤዛ ሆኖ የሚ​ሰጥ ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህ​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢ​ያዬ አድ​ር​ጉት፤”


ሲበሉም ኢየሱስ ኅብስትን አንሥቶ ባረከ፤ ቈርሶም ሰጣቸውና “እንካችሁ፤ ይህ ሥጋዬ ነው፤” አለ።


ሕዝቡም በምድር እንዲቀመጡ አዘዘ። ሰባቱንም እንጀራ ይዞ አመሰገነ፤ ቈርሶም እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ለሕዝቡም አቀረቡ።


አምስቱንም እንጀራ ሁለቱንም ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፤ እንጀራውንም ቈርሶ እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤


ሲበሉም ኢየሱስ ኅብስትን አንሥቶ ባረከ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና “እንካችሁ፥ ብሉ፤ ይህ ሥጋዬ ነው፤” አለ።


እነ​ር​ሱም፥ “መሽ​ቶ​አ​ልና፥ ፀሐ​ይም ተዘ​ቅ​ዝ​ቆ​አ​ልና፥ ከእኛ ጋር እደር” ብለው ግድ አሉት፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሊያ​ድር ገባ።


በሐ​ዋ​ር​ያት ትም​ህ​ር​ትና በአ​ን​ድ​ነት ማዕ​ድን በመ​ባ​ረክ፥ በጸ​ሎ​ትም ጸን​ተው ይኖሩ ነበር።


ሁል​ጊ​ዜም አንድ ልብ ሆነው በቤተ መቅ​ደስ ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በቤ​ትም ኅብ​ስ​ትን ይቈ​ርሱ ነበር፤ በደ​ስ​ታና በልብ ቅን​ን​ነ​ትም ምግ​ባ​ቸ​ውን ይመ​ገቡ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች