Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 24:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እኛ ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ እና​ደ​ርግ ነበር፤ ከዚ​ህም ሁሉ ጋር ይህ ነገር ከሆነ ዛሬ ሦስ​ተኛ ቀን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እኛ ግን እስራኤልን ይቤዣል ብለን ተስፋ ያደረግነው እርሱን ነበር፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እኛ ግን እስራኤልን የሚታደገው እርሱ ነው ብለን ተስፋ አድርገን ነበር፤ ሆኖም ይህ ነገር ከሆነ ሦስተኛው ቀን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እኛ ግን ‘እስራኤልን የሚያድን እርሱ ነው’ ብለን ተስፋ አድርገን ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ ነገር ከተፈጸመ እነሆ፥ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 24:21
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከጽ​ዮን ታዳጊ ይመ​ጣል፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀጢ​አ​ትን ያር​ቃል።


“ይቅር ያለን፥ ለወ​ገ​ኖ​ቹም ድኅ​ነ​ትን ያደ​ረገ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤


ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነች፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ድኅ​ነት ተስፋ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ እርሱ ተና​ገ​ረች።


እነ​ር​ሱም ተሰ​ብ​ስ​በው ሳሉ፥ “ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መን​ግ​ሥ​ትን ትመ​ል​ሳ​ለ​ህን?” ብለው ጠየ​ቁት።


ወይስ ትና​ን​ትና ግብ​ፃ​ዊ​ውን እንደ ገደ​ል​ኸው እኔ​ንም ልት​ገ​ድ​ለኝ ትሻ​ለ​ህን?’


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች