Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሄሮ​ድ​ስም ከሠ​ራ​ዊቱ ጋር አቃ​ለ​ለው፤ አፌ​ዘ​በ​ትም፤ የሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ልብ​ስም አል​ብሶ ወደ ጲላ​ጦስ መልሶ ሰደ​ደው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሄሮድስም ከወታደሮቹ ጋራ ናቀው፤ አፌዙበትም፤ የክብር ልብስ አልብሶም ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሄሮድስም ከሠራዊቱ ጋር ናቀው፤ አፌዘበትም፤ የጌጥ ልብስም አልብሶ ወደ ጲላጦስ መልሶ ላከው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሄሮድስም ከጭፍሮቹ ጋር ሆኖ በንቀት አፌዘበት፤ ጌጠኛ ልብስ አልብሶም ወደ ጲላጦስ መልሶ ላከው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሄሮድስም ከሠራዊቱ ጋር ናቀው ዘበተበትም፥ የጌጥ ልብስም አልብሶ ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 23:11
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምሕ​ረ​ትህ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን ሁሉ ይከ​ተ​ለኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ለረ​ዥም ዘመን እኖር ዘንድ።


ታዳ​ጊህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕይ​ወ​ቱን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ትን፥ በአ​ሕ​ዛብ የተ​ጠ​ላ​ውን የአ​ለ​ቆ​ችን ባርያ ቀድ​ሱት፤ ነገ​ሥ​ታት ያዩ​ታል፤ አለ​ቆ​ችም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብለው ተነ​ሥ​ተው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መር​ጨ​ሃ​ለ​ሁና።”


መል​ኩም የተ​ናቀ፥ ከሰ​ውም ልጆች ሁሉ የተ​ዋ​ረደ፥ የተ​ገ​ረፈ ሰው፥ መከ​ራ​ንም የተ​ቀ​በለ ነው፤ ፊቱ​ንም መል​ሶ​አ​ልና አቃ​ለ​ሉት፥ አላ​ከ​በ​ሩ​ት​ምም።


በዚያ ዘመን የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ የኢየሱስን ዝና ሰማ፤


ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤


ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች፤ ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤


እርሱም መልሶ “ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል፤ ሁሉንም ያቀናል፤ ስለ ሰው ልጅም እንዴት ተብሎ ተጽፎአል? ብዙ መከራ እንዲቀበል እንዲናቅም።


የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎ​ችም ቆመው በብዙ ያሳ​ጡት ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የእ​ሾህ አክ​ሊል ደፍቶ፥ የቀይ ሐር መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ፤ ጲላ​ጦ​ስም፥ “እነሆ፥ ሰው​ዬው” አላ​ቸው።


የወርቅ ቀለበት ያደረገና የጌጥ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢገባ፥ እድፍ ልብስም የለበሰ ድኻ ሰው ደግሞ ቢገባ፥


የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ “አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ፤” ብትሉት፥ ድኻውንም “አንተስ ወደዚያ ቁም” ወይም “ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ፤” ብትሉት፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች