Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 22:61 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

61 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዘወር ብሎ ጴጥ​ሮ​ስን አየው፤ ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” ያለ​ውን የጌ​ታ​ች​ንን ቃል ዐሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

61 ጌታም መለስ ብሎ ጴጥሮስን ተመለከተው፤ ጴጥሮስም፣ “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ብሎ ጌታ የተናገረው ቃል ትዝ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

61 ጌታም ዘወር ብሎ ጴጥሮስን ተመለከተው፤ ጴጥሮስም “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” ያለው የጌታ ቃል ትዝ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

61 በዚህ ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ዞር ብሎ ጴጥሮስን አየው፤ ጴጥሮስም “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” በማለት ጌታ ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አስታወሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

61 ጌታም ዘወር ብሎ ጴጥሮስን ተመለከተው፤ ጴጥሮስም፦ ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ እንዳለው የጌታ ቃል ትዝ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 22:61
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያን​ጊ​ዜም ሰው ራሱን ይነ​ቅ​ፋል፤ እን​ዲ​ህም ይላል፦ ‘እኔ ምን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ? እንደ ኀጢ​አ​ቶ​ችም መጠን አል​ቀ​ጣ​ኝም፤


ታስቢ ዘንድ፥ ታፍ​ሪም ዘንድ፥ ደግ​ሞም ስላ​ደ​ረ​ግ​ሽው ነገር ሁሉ ይቅር ባል​ሁሽ ጊዜ፥ስለ ኀፍ​ረ​ትሽ አፍ​ሽን ትከ​ፍቺ ዘንድ አይ​ቻ​ል​ሽም፤” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እኔም “አም​ል​ኮ​ቴን ትተ​ሃል አልሁ፤ ኤፍ​ሬም ሆይ! እን​ዴት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እስ​ራ​ኤል ሆይ! እን​ዴ​ትስ እደ​ግ​ፍ​ሃ​ለሁ? እን​ዴ​ትስ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በው​ስጤ ተና​ው​ጣ​ለች፤ ምሕ​ረ​ቴም ተገ​ል​ጣ​ለች።


ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፤ በዚች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” አለው።


ጴጥሮስም “ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ።


ወዲያውም ኢየሱስ ከእርሱ ኃይል እንደ ወጣ በገዛ ራሱ አውቆ በሕዝቡ መካከል ዘወር ብሎ “ልብሴን የዳሰሰ ማን ነው?” አለ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፥ ትቸ​ገ​ሪ​ያ​ለ​ሽም፤ ታዘ​ጋ​ጂ​ያ​ለ​ሽም።


እርሱ ግን፥ “ጴጥ​ሮስ ሆይ፥ እል​ሃ​ለሁ፥ ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ እን​ደ​ማ​ታ​ው​ቀኝ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” አለው።


ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! የም​ት​ለ​ውን አላ​ው​ቅም” አለው፤ እር​ሱም ይህን ሲና​ገር ያን​ጊዜ ዶሮ ጮኸ።


ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ውጭ ወጥቶ መራራ ልቅ​ሶን አለ​ቀሰ።


ጌታ​ች​ንም በአ​ያት ጊዜ አዘ​ነ​ላ​ትና፥ “አታ​ል​ቅሺ” አላት።


ዮሐ​ን​ስም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለ​ቱን ጠርቶ፥ “የሚ​መ​ጣው አንተ ነህን? ወይስ ተስፋ የም​ና​ደ​ር​ገው ሌላ አለ?” ብሎ ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ ላካ​ቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፤ “ነፍ​ስ​ህን ስለ እኔ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጣ​ለ​ህን? እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ ሦስት ጊዜ እስ​ክ​ት​ክ​ደኝ ዶሮ አይ​ጮ​ህም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ሱን ለእ​ስ​ራ​ኤል ንስ​ሓን፥ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ስር​የት ይሰጥ ዘንድ ራስም አዳ​ኝም አደ​ረ​ገው፤ በቀ​ኙም አስ​ቀ​መ​ጠው።


እና​ንተ አሕ​ዛብ አስቡ፤ ቀድሞ በሥጋ ሥር​ዐት ነበ​ራ​ችሁ፤ ያል​ተ​ገ​ዘ​ሩም ይሉ​አ​ችሁ ነበር፤ እን​ዲህ የሚ​ሉ​አ​ች​ሁም የተ​ገ​ዘሩ ሰዎች ናቸው፤ ግዝ​ረት ግን በሥጋ ላይ የሚ​ደ​ረግ የሰው እጅ ሥራ ነው።


እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ፤ ንስሓም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሓም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች