Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 22:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እን​ዲ​ሁም ከእ​ራት በኋላ ጽዋ​ዉን አን​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ጽዋ ስለ እና​ንተ በሚ​ፈ​ስ​ሰው ደሜ የሚ​ሆን አዲስ ኪዳን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፤ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈስሰው ደሜ የሚመሠረት አዲስ ኪዳን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ ሰጣቸውና እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚፈጸም አዲስ ኪዳን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፦ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 22:20
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ሁም ኅብ​ስ​ቱን ከተ​ቀ​በሉ በኋላ ጽዋ​ውን አን​ሥቶ፥ “አዲስ ሥር​ዐት የሚ​ጸ​ና​በት ይህ ጽዋ ደሜ ነው እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በም​ት​ጠ​ጡ​በ​ትም ጊዜ አስ​ቡኝ” አላ​ቸው።


ስለ ብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።


ለአንቺም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳንሽ ደም፥ እስሮችሽን ውኃ ከሌለበት ጕድጓድ አውጥቻለሁ።


በዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን ደም ለበ​ጎች ትልቅ እረኛ የሆ​ነ​ውን ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው፥


ሙሴም ደሙን ወስዶ በሕ​ዝቡ ላይ ረጨው፤ በዚህ ቃል ሁሉ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ያደ​ረ​ገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ” አለ።


የአ​ዲስ ኪዳ​ንም መካ​ከ​ለኛ ወደ​ሚ​ሆን ወደ ኢየ​ሱስ፥ ከአ​ቤ​ልም ደም ይልቅ የሚ​ሻ​ለ​ውን ወደ​ሚ​ና​ገር ወደ ተረ​ጨው ደሙ ደር​ሳ​ች​ኋል።


“እነሆ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ከይ​ሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የም​ገ​ባ​በት ወራት ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


የሙ​አች ሰው ኑዛዜ የጸ​ናች ናት፤ ተና​ዛዡ በሕ​ይ​ወት ባለ​በት ጊዜ አት​ጠ​ቅ​ም​ምና።


በመ​ን​ፈስ እንጂ በፊ​ደል ለማ​ይ​ሆን ለአ​ዲስ ሕግ አገ​ል​ጋ​ዮች አደ​ረ​ገን፤ ፊደል ይገ​ድ​ላል፥ መን​ፈስ ግን ሕያው ያደ​ር​ጋል።


ስለ​ዚህ ኢየ​ሱስ ሞትን ተቀ​ብሎ፥ በቀ​ደ​መው ሥር​ዐት ስተው የነ​በ​ሩ​ትን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ወደ ዘለ​ዓ​ለም ርስ​ቱም የጠ​ራ​ቸው ተስ​ፋ​ውን ያገኙ ዘንድ፥ ለአ​ዲ​ሲቱ ኪዳን መካ​ከ​ለኛ ሆነ።


እርሱም “ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች