Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 21:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ይህን ታያ​ላ​ች​ሁን? በእ​ዚህ ቦታ ድን​ጋይ በድ​ን​ጋይ ላይ የማ​ይ​ተ​ው​በ​ትና ሳይ​ፈ​ርስ የማ​ይ​ቀ​ር​በት ዘመን ይመ​ጣል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ይህ የምታዩት ሁሉ ሳይፈርስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ እንደ ተካበ የማይቀርበት ጊዜ ይመጣል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “ይህማ የምታዩት ሁሉ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ የማይቀርበት ዘመን ይመጣል፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ኢየሱስ ግን “ይህ የምታዩት ሁሉ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተነባብሮ የማይቀርበት ጊዜ ይመጣል፤ እነዚህ ድንጋዮች ሁሉ አንድ ቀን ይፈራርሳሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ የማይቀርበት ዘመን ይመጣል አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 21:6
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስም መልሶ “እነዚህን ታላላቅ ሕንጻዎች ታያለህን? ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፤” አለው።


እርሱ ግን መልሶ “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፤” አላቸው።


የጽ​ዮን ተራራ ባድማ ሆና​ለ​ችና፥ ቀበ​ሮ​ዎ​ችም ተመ​ላ​ል​ሰ​ው​ባ​ታ​ልና።


አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ ለሰልፍ እሰበስባለሁ፣ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይነወራሉ፣ የከተማይቱም እኵሌታ ለምርኮ ይወጣል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማ አይጠፋም።


ሊባኖስ ሆይ፥ ደጆችህን ክፈት፥ እሳትም ዝግባዎችህን ትብላ።


አሌፍ። ወርቁ እን​ዴት ደበሰ! ጥሩው ብር እን​ዴት ተለ​ወጠ! የከ​በ​ረው ዕንቍ በጎ​ዳ​ናው ሁሉ እን​ዴት ተበ​ተነ!


“ሞሬ​ታ​ዊው ሚክ​ያስ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን ትን​ቢት ይና​ገር ነበር፤ ለይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ፦ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታ​ረ​ሳ​ለች፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ምድረ በዳ ትሆ​ና​ለች፤ የቤ​ቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆ​ናል ብሎ ተና​ገረ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም፥ “ይህ ቤት እንደ ሴሎ ይሆ​ናል፤ ይችም ከተማ ባድማ ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ኖ​ር​ባ​ትም የለም ብለህ ስለ ምን ትን​ቢት ተና​ገ​ርህ?” ሕዝ​ቡም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ተሰ​ብ​ስ​በው ነበር።


ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ይች​ንም ከተማ ለም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ ርግ​ማን አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ።”


ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።


እነ​ር​ሱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህ መቼ ይደ​ረ​ጋል? ይህስ የሚ​ሆ​ን​በት ጊዜው፥ ምል​ክ​ቱስ ምን​ድን ነው?” ብለው ጠየ​ቁት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች