Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 21:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም ላይ ምል​ክት ይሆ​ናል፤ በም​ድር ላይም አሕ​ዛብ ይጨ​ነ​ቃሉ፤ ከባ​ሕ​ሩና ከሞ​ገዱ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ይሸ​በ​ራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “በፀሓይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ላይ ምልክት ይሆናል፤ ከባሕሩና ከሞገድ ድምፅ የተነሣ፣ በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ይጨነቃሉ፤ ይታወካሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 “በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ላይ ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ በመረበሽ ይጨነቃሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ድንቅ ምልክቶች ይታያሉ፤ በምድርም ላይ ሕዝቦች ሁሉ ከባሕርና ከማዕበሉ አስደንጋጭ ድምፅ የተነሣ ፈርተው ይጨነቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 21:25
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሰ​ማ​ይም ከዋ​ክ​ብ​ትና ኦሪ​ዎን፥ የሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትም ሁሉ ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን አይ​ሰ​ጡም፤ ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ ትጨ​ል​ማ​ለች፤ ጨረ​ቃም በብ​ር​ሃኑ አያ​በ​ራም።


ጣራ​ቸው ይፈ​ር​ሳል፤ ግድ​ግ​ዳ​ቸ​ውም ይወ​ድ​ቃል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራ​ራና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ይነ​ግ​ሣ​ልና፥ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም ፊት ይከ​ብ​ራ​ልና።


ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።


በላይ በሰ​ማይ ተአ​ም​ራ​ትን፥ በታች በም​ድ​ርም ምል​ክ​ቶ​ችን፥ ደምን እሳ​ት​ንና ጢስ​ንም እሰ​ጣ​ለሁ።


ባሕ​ርን የማ​ና​ውጥ፥ ሞገ​ዱም እን​ዲ​ተ​ምም የማ​ደ​ርግ አማ​ላ​ክሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝና፥ ስሜም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኀይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።


“በነዚያ ቀኖች ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤


“ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤


አሕ​ዛ​ብን ከእኛ በታች፥ ወገ​ኖ​ች​ንም ከእ​ግ​ራ​ችን በታች አስ​ገ​ዛ​ልን።


ስድስት ሰዓትም በሆነ ጊዜ፥ እስከ ዘጠኝ ሰዓት በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።


ምድ​ሪ​ቱን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ባዶ ነበ​ረች፤ ሰማ​ያ​ት​ንም ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ ብር​ሃ​ንም አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም።


በዚ​ያም ቀን እንደ ባሕር መት​መም ይተ​ም​ሙ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወደ ምድ​ርም ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማን ያያሉ፤ ይጨ​ነ​ቃ​ሉም።


ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።


ከእነርሱም ሁሉ የተሻለው እርሱ እንደ አሜከላ ነው፥ ከሁሉም ቅን የሆነው እንደ ኵርንችት ነው፥ ጠባቆችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቶአል፥ አሁን ይሸበራሉ።


እንደ ውኃ ለሞሉ፥ ከተ​ራራ በመ​ከ​ታ​ተል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ የውኃ ፈሳሽ ለሆ​ኑም ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ ወዮ​ላ​ቸው!


በሰ​ይፍ ስለት ይወ​ድ​ቃሉ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይማ​ረ​ካሉ፤ የአ​ሕ​ዛብ ጊዜ​ያ​ቸው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ አሕ​ዛብ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይረ​ግ​ጡ​አ​ታል።


በዓ​ለም ላይ ከሚ​መ​ጣው ፍር​ሀ​ትና ሽብር የተ​ነ​ሣም የሰ​ዎች ነፍስ ትዝ​ላ​ለች፤ ያን​ጊዜ የሰ​ማ​ያት ኀይል ይና​ወ​ጣ​ልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች