Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 20:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እር​ሱም፥ “እን​ኪ​ያስ የቄ​ሣ​ርን ለቄ​ሣር፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጡ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እርሱም፣ “እንግዲያውስ የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እርሱም “እንግዲያውስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ኢየሱስም “እንግዲያውስ የንጉሡን ለንጉሡ፥ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እርሱም፦ እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 20:25
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ብት​በ​ሉም፥ ብት​ጠ​ጡም የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር አድ​ር​ጉት።


ጴጥ​ሮ​ስና ሐዋ​ር​ያ​ትም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ለሰው ከመ​ታ​ዘዝ ይልቅ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​ዘዝ ይገ​ባል።


ኢየሱስም መልሶ “የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ፤” አላቸው። በእርሱም ተደነቁ።


“የቄሳር ነው፤” አሉት። በዚያን ጊዜ “እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ፤” አላቸው።


ነገር ግን እንዳናሰናክላቸው፥ ወደ ባሕር ሂድና መቃጥን ጣል፤ መጀመሪያም የሚወጣውን ዓሣ ውሰድና አፉን ስትከፍት እስታቴር ታገኛለህ፤ ያን ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ስጣቸው፤” አለው።


ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፥ ከእነርሱ ለአንዱ ስንኳ እንቢ አትበል።


ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።


አም​ጥ​ተ​ውም አሳ​ዩት፤ “መልኩ፥ ጽሕ​ፈ​ቱስ የማ​ነው?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የቄ​ሣር ነው” ብለው መለ​ሱ​ለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች