Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከዚ​ህም በኋላ መላ​እ​ክት ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ ወደ ሰማይ በዐ​ረጉ ጊዜ እነ​ዚያ እረ​ኞች ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “እስከ ቤተ ልሔም እን​ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የገ​ለ​ጠ​ል​ንን ይህን ነገር እን​ወቅ” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 መላእክቱ ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ ከወጡ በኋላ እረኞቹ፣ “ጌታ የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንድናይ ወደ ቤተ ልሔም እንሂድ” ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው፦ “እንግዲህ እስከ ቤተልሔም ድረስ እንሂድ፤ ጌታም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ፤” ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 መላእክቱ ተለይተዋቸው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ እረኞቹ እርስ በርሳቸው፦ “እንግዲህ ወደ ቤተልሔም እንሂድ፤ አሁን የተፈጸመውንና ጌታ የገለጠልንን ነገር እንይ” ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው፦ እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 2:15
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚ​ህም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኤል​ያ​ስን በዐ​ውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ በሚ​ያ​ወ​ጣው ጊዜ ኤል​ያ​ስና ኤል​ሳዕ ከጌ​ል​ጌላ ተነ​ሥ​ተው ሄዱ።


ሁለ​ቱም እየ​ተ​ነ​ጋ​ገሩ ሲሄዱ፥ እነሆ፥ የእ​ሳት ሰረ​ገ​ላና የእ​ሳት ፈረ​ሶች በሁ​ለቱ መካ​ከል ገብ​ተው ከፈ​ሉ​አ​ቸው፤ ኤል​ያ​ስም በዐ​ውሎ ነፋስ ንው​ጽ​ው​ጽታ ወደ ሰማይ ወጣ።


ዘሩ በም​ድር ላይ ኀያል ይሆ​ናል፤ የጻ​ድ​ቃን ትው​ል​ዶች ይባ​ረ​ካሉ።


ሙሴም፥ “ልሂ​ድና ቍጥ​ቋ​ጦው ስለ​ምን አል​ተ​ቃ​ጠ​ለም? ይህን ታላቅ ራእይ ልይ” አለ።


ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፤ እነሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።


“ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት፥ ሰላ​ምም በም​ድር፥ ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ” ይሉ ነበር።


ፈጥ​ነ​ውም ሄዱ፤ ማር​ያ​ም​ንና ዮሴ​ፍን አገ​ኙ​አ​ቸው፤ ሕፃ​ኑ​ንም በበ​ረት ውስጥ ተኝቶ አገ​ኙት።


እየ​ባ​ረ​ካ​ቸ​ውም ራቃ​ቸው፤ ወደ ሰማ​ይም ዐረገ።


እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች