Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ጌታ​ውም፦ መል​ካም፥ አንተ በጎ አገ​ል​ጋይ በጥ​ቂት የታ​መ​ንህ ስለ​ሆ​ንህ በብዙ ላይ እሾ​ም​ሃ​ለሁ፤ በዐ​ሥሩ ከተ​ሞች ላይ ተሾም አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ጌታውም፣ ‘አንተ ታማኝ ባሪያ፣ መልካም አድርገሃል፤ በትንሽ ነገር ታማኝ ሆነህ ስለ ተገኘህ፣ በዐሥር ከተሞች ላይ ሥልጣን ተሰጥቶሃል’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እርሱም ‘መልካም፥ አንተ በጎ አገልጋይ፥ በጥቂት ነገር የታመንህ ስለ ሆንክ በዐሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ፤’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ጌታውም ‘አንተ መልካም አገልጋይ! ደግ አደረግህ፤ በትንሽ ነገር ስለ ታመንህ እኔ ደግሞ በዐሥር ከተሞች ላይ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እርሱም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ባሪያ፥ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በአሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ይሁንልህ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 19:17
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም በጌ​ታው ፊት ሞገ​ስን አገኘ፤ እር​ሱ​ንም ደስ ያሰ​ኘው ነበር፤ በቤ​ቱም ላይ ሾመው፤ ያለ​ው​ንም ሁሉ በእጁ ሰጠው።


ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፥ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ፤’ አለው።


“በጥ​ቂት የሚ​ታ​መን በብዙ ይታ​መ​ናል፤ በጥ​ቂት የሚ​ያ​ም​ፅም በብ​ዙም ቢሆን ያም​ፃል።


አን​ደ​ኛ​ውም መጥቶ፦ አቤቱ፥ ምና​ንህ ዐሥር ነበር፤ እነሆ ዐሥር ምናን አት​ር​ፌ​አ​ለሁ አለው።


ሁለ​ተ​ኛ​ውም መጥቶ፦ አቤቱ፥ ምና​ንህ አም​ስት ነበር፤ አም​ስት አት​ር​ፌ​አ​ለሁ አለው።


በመ​ን​ግ​ሥቴ በማ​ዕዴ ትበ​ሉና ትጠጡ ዘንድ፥ በወ​ን​በ​ሮ​ችም ተቀ​ም​ጣ​ችሁ በዐ​ሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ትፈ​ርዱ ዘንድ።”


ዳሩ ግን አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ነት በስ​ውር ነው፤ መገ​ዘ​ርም በመ​ን​ፈስ የልብ መገ​ዘር እንጂ በኦ​ሪት ሥር​ዐት አይ​ደ​ለም፤ ምስ​ጋ​ና​ውም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ ከሰው አይ​ደ​ለም።


ጊዜው ሳይ​ደ​ርስ ዛሬ ለምን ትመ​ረ​ም​ራ​ላ​ቸሁ? በጨ​ለማ ውስጥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያ​በራ፥ የል​ብን አሳ​ብም የሚ​ገ​ልጥ ጌታ​ችን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊዜ ሁሉም ዋጋ​ውን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቀ​በ​ላል።


ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን መዳን ከዘላለም ክብር ጋር እንዲያገኙ ስለ ተመረጡት በነገር ሁሉ እጸናለሁ።


የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ው​ነት ቤትህ፥ የአ​ባ​ት​ህም ቤት፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊቴ እን​ዲ​ኖር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያከ​በ​ሩ​ኝን አከ​ብ​ራ​ለ​ሁና፥ የና​ቁ​ኝም ይና​ቃ​ሉና ይህ አይ​ሆ​ን​ል​ኝም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች