Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 17:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ሁለት ሰዎች በአ​ንድ አልጋ ይተ​ኛሉ፤ አን​ዱን ይወ​ስ​ዳሉ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ይተ​ዋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 እላችኋለሁ፤ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ ዐልጋ ይተኛሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሁለተኛውም ይቀራል እላችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ይተኛሉ፤ ከእነርሱም አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል እላችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 እላችኋለሁ፥ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 17:34
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤


እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።


“ወደ ጠባቡ በር ትገቡ ዘንድ በርቱ፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሊገቡ የሚሹ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ግን አይ​ች​ሉም።


እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ።


ለራ​ስህ ታላ​ላቅ ነገ​ሮ​ችን ትፈ​ል​ጋ​ለ​ህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ እነሆ ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ለ​ሁና አት​ፈ​ል​ጋ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን በሄ​ድ​ህ​በት ስፍራ ሁሉ ነፍ​ስ​ህን እንደ ምርኮ አድ​ርጌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”


እነሆ የቀ​ድ​ሞው ነገር ተፈ​ጸመ፤ አዲስ ነገ​ር​ንም እና​ገ​ራ​ለሁ፤ አስ​ቀ​ድ​ሞም ሳይ​ነ​ገር እር​ሱን አስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በው​ኆች ላይ ነው። የክ​ብር አም​ላክ አን​ጐ​ደ​ጐደ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብዙ ውኆች ላይ ነው።


ፊት​ህን ከእኔ አት​መ​ልስ፥ ተቈ​ጥ​ተህ ከባ​ሪ​ያህ ፈቀቅ አት​በል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አት​ጣ​ለ​ኝም፥ አም​ላ​ኪ​ዬና መድ​ኀ​ኒቴ ሆይ፥ ቸል አት​በ​ለኝ።


አይ​ደ​ለም፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ንስሓ ካል​ገ​ባ​ችሁ ሁላ​ችሁ እንደ እነ​ርሱ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”


አይ​ደ​ለም፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ንስሓ ካል​ገ​ባ​ችሁ ሁላ​ችሁ እንደ እነ​ርሱ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።


ጴጥሮስም “ሁሉም ቢሰናከሉ እኔ ግን ከቶ አልሰናከልም፤” አለው።


ነፍ​ሱን ሊያ​ድ​ናት የሚ​ወድ ይጣ​ላት፤ ስለ እኔ ነፍ​ሱን የሚ​ጥ​ላ​ትም ያድ​ና​ታል።


ሁለት ሴቶ​ችም በአ​ንድ ወፍጮ ይፈ​ጫሉ፤ አን​ዲ​ቱን ይወ​ስ​ዳሉ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ይተ​ዋሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች