Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 17:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እን​ኋት፥ በዚህ ናት፤ ወይም እነ​ኋት፥ በዚያ ናት አይ​ሉ​አ​ትም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትስ እነ​ኋት፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ናት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሰዎችም፣ ‘እዚህ ነው’ ወይም ‘እዚያ ነው’ ማለት አይችሉም፤ እነሆ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ደግሞም ‘ይችትና!’ ወይም ‘ያቻትና!’ የምትባል አይደለችም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እንዲሁም ‘እነሆ፥ እዚህ ናት ወይም እዚያ ናት’ የምትባል አይደለችም፤ እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ነች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ደግሞም፦ እንኋት በዚህ ወይም፦ እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 17:21
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ጽድ​ቅና ሰላም፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የሆነ ደስታ ነው እንጂ መብ​ልና መጠጥ አይ​ደ​ለ​ምና።


በዚያን ጊዜም ማንም ‘እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፤’ ወይም ‘እነሆ፥ ከዚያ አለ፤’ ቢላችሁ አትመኑ፤


ዛሬ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ምክር የክ​ብር ባለ​ጸ​ግ​ነት በአ​ሕ​ዛብ ላይ እን​ዲ​ገ​ል​ጽ​ላ​ቸው ለፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸው ለቅ​ዱ​ሳን ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው፤ የም​ን​ከ​ብ​ር​በት አለ​ኝ​ታ​ችን በእ​ና​ንተ አድሮ ያለ ክር​ስ​ቶስ ነውና።


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ብዙ​ዎች እኔ ክር​ስ​ቶስ ነኝ፤ ጊዜ​ውም ደር​ሶ​አል እያሉ በስሜ ይመ​ጣ​ሉና እን​ዳ​ያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ተከ​ት​ላ​ችሁ አት​ሂዱ።


እነሆ፥ በዚህ ነው፥ ወይም እነሆ፥ በዚያ ነው ቢሉ​አ​ችሁ አት​ውጡ፤ አት​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውም።


ዮሐ​ን​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ በውኃ አጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነገር ግን እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ቆሞ​አል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእኔ መን​ግ​ሥት ከዚህ ዓለም አይ​ደ​ለ​ችም፤ መን​ግ​ሥ​ቴስ በዚህ ዓለም ብት​ሆን ኖሮ ለአ​ይ​ሁድ እን​ዳ​ል​ሰጥ አሽ​ከ​ሮች በተ​ዋ​ጉ​ልኝ ነበር፤ አሁ​ንም መን​ግ​ሥቴ ከዚህ አይ​ደ​ለ​ችም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች