Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 16:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 አብ​ር​ሃ​ምም፦ ‘ሙሴ​ንና ነቢ​ያ​ትን ካል​ሰ​ሙማ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነሣ ቢኖ​ርም እንኳ አይ​ሰ​ሙ​ትም፤ አያ​ም​ኑ​ት​ምም’ አለው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 “አብርሃምም፣ ‘ሙሴንና ነቢያትን የማይሰሙ ከሆነ፣ አንድ ሰው ከሙታን ቢነሣ እንኳ አያምኑም’ አለው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ‘ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ሰው ቢነሣ አያምኑም፤’ አለው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 አብርሃምም ‘የሙሴና የነቢያት መጻሕፍት የሚሉትን ካልሰሙማ አንድ ሰው ከሞት ተነሥቶ ቢነግራቸውም አያምኑትም’ አለው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 16:31
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የያ​ፌ​ትን ሀገር ያስፋ፤ በሴ​ምም ድን​ኳን ይደር፤ ከነ​ዓ​ንም ለእ​ርሱ ባሪያ ይሁን።”


እር​ሱም፦ ‘የለም፤ አባት አብ​ር​ሃም ሆይ፥ ከሙ​ታን አንዱ ወደ እነ​ርሱ ካል​ሄ​ደና ካል​ነ​ገ​ራ​ቸው ንስሓ አይ​ገ​ቡም’ አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “መሰ​ና​ክል ግድ ይመ​ጣል፤ ነገር ግን መሰ​ና​ክ​ልን ለሚ​ያ​መ​ጣት ሰው ወዮ​ለት።


ሙሴ የጻ​ፈ​ውን ካላ​መ​ና​ችሁ ግን የእ​ኔን ቃል እን​ዴት ታም​ና​ላ​ችሁ?”


ጳው​ሎ​ስም ወደ ምኵ​ራብ ገብቶ በግ​ልጥ አስ​ተ​ማረ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥት እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸ​ውና እያ​ሳ​መ​ና​ቸው ሦስት ወር ቈየ።


አግ​ሪ​ጳም ጳው​ሎ​ስን፥ “አሁ​ንስ ወደ ክር​ስ​ቲ​ያ​ን​ነት ልታ​ገ​ባኝ ጥቂት ብቻ ቀር​ቶ​ሃል” አለው።


ከዚ​ህም በኋላ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጡ​በ​ትን ቀን ቀጠ​ሩ​ትና ብዙ​ዎች ወዳ​ረ​ፈ​በት ወደ እርሱ መጡ፤ ከጥ​ዋ​ትም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እየ​መ​ሰ​ከረ ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱ​ስም ከሙሴ ኦሪ​ትና ከነ​ቢ​ያት እየ​ጠ​ቀሰ ነገ​ራ​ቸው።


ወን​ጌ​ላ​ችን የተ​ሰ​ወረ ቢሆ​ንም እንኳ፥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ባ​ቸው ለሚ​ጠ​ፉት ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ዐው​ቀን ሰዎ​ችን እና​ሳ​ም​ና​ለን፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እኛ የተ​ገ​ለ​ጥን ነን፤ እን​ዲ​ሁም በል​ቡ​ና​ችሁ የተ​ገ​ለ​ጥን እንደ ሆን እን​ታ​መ​ና​ለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች