Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 16:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በቍ​ስል ሕመም ተይዞ በባ​ለ​ጸ​ጋው ደጅ የወ​ደቀ አል​ዓ​ዛር የሚ​ባል አንድ ድሃም ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በአንጻሩም፣ መላ ሰውነቱ በቍስል የተወረረ አንድ አልዓዛር የሚባል ድኻ በዚህ ሀብታም ሰው ደጃፍ ይተኛ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 አልዓዛር የሚባል አንድ ድኻ ሰው ደግሞ በቁስል ተወርሶ በደጁ ተኝቶ ነበር፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 መላ ሰውነቱ በቊስል የተወረሰ አልዓዛር የሚባል አንድ ድኻ ደግሞ በሀብታሙ ቤት ደጃፍ ተኝቶ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 አልዓዛርም የሚባል አንድ ድሀ በቍስል ተወርሶ በደጁ ተኝቶ ነበር፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 16:20
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ናቱ ማኅ​ፀ​ንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተ​ወ​ለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደ መቅ​ደ​ስም ከሚ​ገ​ቡት ምጽ​ዋት ይለ​ምን ዘንድ ሁል​ጊዜ እየ​ተ​ሸ​ከሙ መል​ካም በሚ​ል​ዋት በመ​ቅ​ደስ ደጃፍ ያስ​ቀ​ም​ጡት ነበር።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና።


ከባ​ለ​ጸ​ጋው ማዕድ የሚ​ወ​ድ​ቀ​ው​ንም ፍር​ፋሪ ሊመ​ገብ ይመኝ ነበር፤ ውሾ​ችም እየ​መጡ ቍስ​ሉን ይል​ሱት ነበር።


ሰይ​ጣ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወጣ፥ ኢዮ​ብ​ንም ከእ​ግሩ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቍስል መታው።


ችግ​ረ​ኛ​ውን ከመ​ሬት ያነ​ሣ​ዋል፤ ምስ​ኪ​ኑ​ንም ከጕ​ድፍ ያነ​ሣ​ዋል፤ ከሕ​ዝቡ መኳ​ን​ንት ጋር ያስ​ቀ​ም​ጠው ዘንድ፥ የክ​ብ​ር​ንም ዙፋን ያወ​ር​ሰው ዘንድ።


በገ​ለ​ዓድ መድ​ኀ​ኒት የለ​ምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለ​ምን? የወ​ገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አል​ሆ​ነም?


ከእ​ግር ጫማ አን​ሥቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለ​ውም፤ ቍስ​ልና እበጥ የሚ​መ​ግ​ልም ነው፤ አል​ፈ​ረ​ጠም፤ አል​ተ​ጠ​ገ​ነ​ምም፤ በዘ​ይ​ትም አል​ለ​ዘ​በም።


አን​ተም የዘ​ን​ዶ​ውን ራሶች ቀጠ​ቀ​ጥህ፤ ለኢ​ት​ዮ​ጵያ ሕዝ​ብም ምግ​ባ​ቸ​ውን ሰጠ​ሃ​ቸው።


በግፍ የሚ​ጠ​ሉኝ በላዬ ደስ አይ​በ​ላ​ቸው፥ በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉ​ኝና በዐ​ይ​ና​ቸው የሚ​ጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኝም።


የማ​ር​ያ​ምና የእ​ኅቷ የማ​ርታ መን​ደር በሚ​ሆን በቢ​ታ​ንያ ስሙ አል​ዓ​ዛር የሚ​ባል የታ​መመ አንድ ሰው ነበር።


ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት “ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ፤” አለች።


“አንድ ባለ​ጸጋ ሰው ነበረ፤ ቀይ ሐርና ነጭ ሐር፥ እጅ​ግም ቀጭን ልብስ ይለ​ብስ ነበር፤ ዘወ​ት​ርም ተድ​ላና ደስታ ያደ​ርግ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች