Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 15:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እሪ​ያ​ዎች ከሚ​መ​ገ​ቡት ተረ​ን​ቃ​ሞም ይጠ​ግብ ዘንድ ተመኘ፤ ግን የሚ​ሰ​ጠው አል​ነ​በ​ረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ዐሣማዎቹ የሚመገቡትን ዐሠር እንኳ ለመብላት ይመኝ ነበር፤ ነገር ግን ይህን እንኳ የሚሰጠው ሰው አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ዐሣማዎችም ከሚበሉት ፍልፋይ ለመጥገብ ይመኝ ነበር፤ የሚሰጠውም አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ዐሣማዎቹ ከሚመገቡት ብጣሪ ዐሠር ሆዱን ለመሙላት ይመኝ ነበር፤ ግን ይህንኑ እንኳ የሚሰጠው አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እሪያዎችም ከሚበሉት አሰር ሊጠግብ ይመኝ ነበር፥ የሚሰጠውም አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 15:16
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤፍ​ሬም በሐ​ሰት፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ይሁ​ዳም በተ​ን​ኰል ከበ​ቡኝ፤ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐወ​ቃ​ቸው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቅዱስ ሕዝብ ተባሉ።


ሄ። የጣ​ፈጠ ነገር ይበሉ የነ​በሩ በመ​ን​ገድ ጠፉ፤ በቀይ ግምጃ ያድጉ የነ​በሩ የፍግ ክምር አቀፉ።


እን​ግ​ዲህ ልባ​ቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ነፍ​ሱን ለማ​ዳን የሚ​ችል ማንም እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚ​ልም እን​ደ​ሌለ ተመ​ል​ከቱ።


ሰው​ነቴ በላዬ አለ​ቀ​ች​ብኝ፥ ልቤም በው​ስጤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ።


እና​ንተ የኃ​ጥ​ኣን ልጆች፥ የዘ​ማ​ው​ያ​ንና የጋ​ለ​ሞ​ታ​ዪቱ ዘር፥ ወደ​ዚህ ቅረቡ።


ገን​ዘ​ብን እን​ጀራ ላይ​ደለ፥ የድ​ካ​ማ​ች​ሁ​ንም ዋጋ ለማ​ያ​ጠ​ግብ ነገር ለምን ትመ​ዝ​ና​ላ​ችሁ? አድ​ም​ጡኝ፤ በረ​ከ​ት​ንም ብሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ደስ ይበ​ለው።


አቤቱ፥ ተነሥ፥ በቀ​ሌ​ንም ተበ​ቀል፤ ሰነ​ፎች ሁል​ጊዜ የተ​ገ​ዳ​ደ​ሩ​ህን ዐስብ።


በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።


ሄዶም ከዚያ ሀገር ሰዎች ለአ​ንዱ ተቀ​ጠረ፤ እሪ​ያ​ዎ​ች​ንም ይጠ​ብቅ ዘንድ ወደ እር​ሻው ቦታ ሰደ​ደው።


በል​ቡም እን​ዲህ ብሎ ዐሰበ፦ እህል የሚ​ተ​ር​ፋ​ቸው የአ​ባቴ ሠራ​ተ​ኞች ምን ያህል ናቸው? እኔ ግን በዚህ በረ​ኃብ ልሞት ነው።


እየ​ዞሩ የሚ​ለ​ም​ኑና የሚ​በሉ በቅ​ል​ው​ጥም የሚ​ኖሩ ወራ​ዶች፥ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና ከበጎ ነገ​ሮች ሁሉ የተ​ቸ​ገሩ ናቸው። ከታ​ላቅ ረኃ​ብም የተ​ነሣ ጨው ጨው የሚ​ለ​ውን የእ​ን​ጨት ሥር ይበ​ላሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች