Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 14:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የጠ​ራ​ው​ንም እን​ዲህ አለው፥ “በበ​ዓል ምሳ ወይም ራት በም​ታ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ወዳ​ጆ​ች​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን፥ ዘመ​ዶ​ች​ህ​ንና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ህን፥ ባለ​ጸ​ጎች ባል​ን​ጀ​ሮ​ች​ህ​ንም አት​ጥራ፤ እነ​ር​ሱም ይጠ​ሩ​ሃ​ልና፤ ብድ​ርም ይሆ​ን​ብ​ሃ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ኢየሱስም የጋበዘውን ሰው ደግሞ እንዲህ አለው፤ “የምሳ ወይም የእራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ፣ በዐጸፋው እንዳይጋብዙህና ብድራትን እንዳይመልሱልህ፣ ወዳጆችህን ወይም ወንድሞችህን ወይም ዘመዶችህን ወይም ከበርቴ ጎረቤቶችህን አትጋብዝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የጠራውንም ደግሞ እንዲህ አለው “ምሳ ወይም እራት ባሰናዳህ ጊዜ፥ ምናልባት እነርሱም በተራቸው እንዳይጠሩህ፥ እንዳይክሱህም፥ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ሀብታም ጎረቤቶችህንም አትጥራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ኢየሱስ ጋባዡን ሰው ደግሞ እንዲህ አለው፦ “የምሳ ወይም የእራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ብድራቸውን ለመመለስ በተራቸው የሚጋብዙህን ወዳጆችህን፥ ወንድሞችህን፥ ዘመዶችህን፥ ሀብታሞች ጐረቤቶችህንም አትጥራ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የጠራውንም ደግሞ እንዲህ አለው፦ ምሳ ወይም እራት ባደረግህ ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ ብድራትም እንዳይመልሱልህ፥ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ባለ ጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 14:12
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባለጠጎች ወዳጆች ድሆች ወዳጆችን ይጠላሉ፤ የባለጠጎች ወዳጆች ግን ብዙዎች ናቸው።


ድሃን የሚቀማ ገንዘቡን ብዙ ያደርግለታል፥ በችግሩ ጊዜም ለባለጠጋ ይሰጣል።


የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?


የተ​ራ​ቡ​ትን ከበ​ረ​ከቱ አጠ​ገ​ባ​ቸው፤ ባለ​ጠ​ጎ​ች​ንም ባዶ እጃ​ቸ​ውን ሰደ​ዳ​ቸው።


ዘመ​ዶ​ች​ዋና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ዋም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ቱን እን​ዳ​በ​ዛ​ላት በሰሙ ጊዜ ከእ​ር​ስዋ ጋር ደስ አላ​ቸው።


ራሱን ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም ያሚ​ያ​ዋ​ርድ ከፍ ይላ​ልና።”


ነገር ግን በበ​ዓል ምሳ በም​ታ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ድሆ​ች​ንና ጦም አዳ​ሪ​ዎ​ችን፥ ዕው​ሮ​ችን፥ እጅና እግ​ርም የሌ​ላ​ቸ​ውን ጥራ።


ልጆች እንደ መሆ​ና​ችሁ፥ ይህን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ ላይ ስለ​ሚ​ገ​ባኝ ብድ​ራቴ እና​ንተ ፍቅ​ራ​ች​ሁን አስ​ፉ​ልኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች