Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 14:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ህም በኋላ ሄዶ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን አለ​ቆች ወደ አንዱ ቤት በሰ​ን​በት ቀን እህል ሊበላ ገባ፤ እነ​ርሱ ግን ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አንድ ሰንበት ቀን፣ ኢየሱስ ምግብ ሊበላ ከፈሪሳውያን አለቆች አንዱ ወደ ነበረ ሰው ቤት በገባ ጊዜ፣ ሰዎች በዐይን ይከታተሉት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በሰንበትም ቀን ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት ምግብ ሊበላ በገባ ጊዜ እነርሱ ይጠባበቁት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በሰንበት ቀን፥ ኢየሱስ ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት ምሳ ሊበላ ገባ፤ ፈሪሳውያን እርሱ የሚያደርገውን ለማየት ይጠባበቁት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሰንበትም ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት እንጀራ ሊበላ በገባ ጊዜ እነርሱ ይጠባበቁት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 14:1
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወ​ከች፤ ስለ​ዚህ አቤቱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ምድር፥ በአ​ር​ሞ​ን​ኤ​ምም በታ​ናሹ ተራራ አስ​ብ​ሃ​ለሁ።


እን​ዲህ በሕ​ይ​ወቴ ዘመን አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ በአ​ን​ተም ስም እጆ​ችን አነ​ሣ​ለሁ።


ሣርን እንደሚበላ ይበላል፥ ይጠጣልም፤ ወደ አንተም አታስገባው፥ ከእርሱ ጋርም እንጀራን አትብላ፥ ብላ፥ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም።


እንግዲህ ሰው ከበግ ይልቅ እንደምን አይበልጥም! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል፤” አላቸው።


ሊከሱትም በሰንበት ይፈውሰው እንደ ሆነ ይጠባበቁት ነበር።


ይህ​ንም ሲነ​ግ​ራ​ቸው አንድ ፈሪ​ሳዊ በእ​ርሱ ዘንድ ምሳ እን​ዲ​በላ ለመ​ነው፤ ገብ​ቶም ለምሳ ተቀ​መጠ።


እነ​ሆም፥ ሆዱ የተ​ነፋ አንድ ሰው በፊቱ ነበር።


ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት መቼ ትመ​ጣ​ለች?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት በመ​ጠ​ባ​በቅ አት​መ​ጣም።


ከእ​ነ​ር​ሱም ተለ​ይ​ተው ከሄዱ በኋላ፥ የሚ​ጠ​ባ​በ​ቁ​ትን አዘ​ጋ​ጁ​ለት፤ በአ​ነ​ጋ​ገ​ሩም ያስ​ቱት ዘንድ ወደ መኳ​ን​ን​ትና ወደ መሳ​ፍ​ንት አሳ​ል​ፈው ሊሰ​ጡት ራሳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ጻ​ድቁ ሰላ​ዮ​ችን ወደ እርሱ ላኩ።


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም የሚ​ከ​ሱ​በት ምክ​ን​ያት ያገኙ ዘንድ፥ በሰ​ን​በት ይፈ​ው​ሰው እንደ ሆነ ብለው ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበር።


ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን የአ​ይ​ሁድ አለቃ የሆነ ኒቆ​ዲ​ሞስ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ።


በሸ​ን​ጎ​ዉም በሕ​ዝቡ ሁሉ ዘንድ የከ​በረ የኦ​ሪት መም​ህር ስሙን ገማ​ል​ያል የሚ​ሉት አንድ ፈሪ​ሳዊ ተነሣ፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ከጉ​ባ​ኤዉ ጥቂት ፈቀቅ እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ጉ​አ​ቸው አዘዘ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች