Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 13:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አቤቱ አፈር ቈፍሬ በሥሯ እስከ አስ​ታ​ቅ​ፋት፥ ፍግም እስከ አፈ​ስ​ባት ድረስ የዘ​ን​ድ​ሮን እንኳ ተዋት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ ‘ጌታ ሆይ፤ ዙሪያዋን እስክኰተኵትላትና ፍግ እስከማደርግላት ድረስ ለዘንድሮ ብቻ ተዋት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እርሱ ግን መልሶ፥ ጌታ ሆይ! ዙሪያዋን እስክኰተኩትላትና ፍግ እስካፈስላት ድረስ ይህችን ዓመት ደግሞ ተዋት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አትክልተኛው ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ ‘ጌታዬ ሆይ! እስቲ ለዚህ ዓመት ደግሞ ተዋት፤ ዙሪያዋን ኰትኲቼ ማዳበሪያ አደርግላታለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እርሱ ግን መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ ዙሪያዋን እስክኰተኵትላትና ፋንድያ እስካፈስላት ድረስ በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 13:8
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ር​ከ​ቦች ወደ ባሕር የሚ​ወ​ርዱ፥ በብዙ ውኃ ሥራ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ፥


“አቤቱ በፊ​ት​ህስ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ ሕዝብ አን​ገተ ደን​ዳና ነውና ጌታዬ ከእኛ ጋር ይሂድ፤ ጠማ​ማ​ነ​ታ​ች​ንን፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ን​ንና በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ ለአ​ን​ተም እን​ሆ​ና​ለን” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙ​ኤል በፊቴ ቢቆ​ሙም፥ ልቤ ወደ​ዚህ ሕዝብ አያ​ዘ​ነ​ብ​ልም፤ እነ​ዚ​ህን ሕዝ​ቦች ከፊቴ አባ​ር​ራ​ቸው፤ ይውጡ።


ለሰ​ው​ነቴ ጕድ​ጓ​ድን ቈፍ​ረ​ዋል፤ በውኑ በመ​ል​ካም ፈንታ ክፉ ይመ​ለ​ሳ​ልን? ስለ እነ​ርሱ በመ​ል​ካም እና​ገር ዘንድ፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ትመ​ልስ ዘንድ በፊ​ትህ እንደ ቆምሁ አስብ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች ካህ​ናት በወ​ለ​ሉና በም​ሥ​ዋዑ መካ​ከል እያ​ለ​ቀሱ፥ “አቤቱ! ለሕ​ዝ​ብህ ራራ፤ አሕ​ዛ​ብም ይገ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ ርስ​ት​ህን ለማ​ላ​ገጫ አሳ​ል​ፈህ አት​ስጥ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል፦ አም​ላ​ካ​ቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ?” ይበሉ።


የወ​ይ​ኑን ጠባ​ቂም፦ “የዚ​ችን በለስ ፍሬ ልወ​ስድ ስመ​ላ​ለስ እነሆ፥ ሦስት ዓመት ነው፤ አላ​ገ​ኘ​ሁም፤ እን​ግ​ዲ​ህስ ምድ​ራ​ች​ንን እን​ዳ​ታ​ቦ​ዝን ቍረ​ጣት” አለው።


ምና​ል​ባት ለከ​ርሞ ታፈራ እንደ ሆነ፥ ያለ​ዚያ ግን እን​ቈ​ር​ጣ​ታ​ለን።”


ለም​ድ​ርም ቢሆን፥ ለፍግ መቆ​ለ​ያም ቢሆን አይ​ረ​ባም፤ ነገር ግን ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ የሚ​ሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”


ወን​ድ​ሞች፥ የእ​ኔስ የልቤ ምኞት፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የማ​ቀ​ር​በው ጸሎ​ትም እስ​ራ​ኤል እን​ዲ​ድኑ ነው።


ይህም በዚህ ዘመ​ዶ​ችን አስ​ቀ​ና​ቸው እንደ ሆነ፥ ከእ​ነ​ርሱ ወገን የሆ​ኑ​ት​ንም አድን እንደ ሆነ ነው።


ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሓ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች