Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እን​ዲ​ህም ብሎ መሰ​ለ​ላ​ቸው፥ “አንድ ሰው በታ​ወ​ቀች በወ​ይኑ ቦታ ውስጥ በለስ ነበ​ረ​ችው፤ ፍሬ​ዋን ሊወ​ስድ ወደ እር​ስዋ ሄዶ አላ​ገ​ኘም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ደግሞም እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ተናገረ፤ “አንድ ሰው በወይኑ ዕርሻ ቦታ የተተከለች አንዲት የበለስ ተክል ነበረችው፤ እርሱም ፍሬ ሊፈልግባት መጥቶ ምንም አላገኘም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ይህንንም ምሳሌ ነገራቸው፦ “አንድ ሰው በወይን አትክልቱ ቦታ የተተከለች በለስ ነበረችው፤ በእርሷም ፍሬ ፈልጎ ቢመጣ ምንም አላገኘም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፦ “አንድ ሰው በወይን ተክሉ ቦታ ውስጥ የተተከለች አንዲት የበለስ ዛፍ ነበረችው፤ ከዚያች የበለስ ዛፍ ፍሬ አገኛለሁ ብሎ ቢሄድ ምንም ሳያገኝ ቀረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ይህንም ምሳሌ አለ፦ ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው፥ ፍሬም ሊፈልግባት መጥቶ ምንም አላገኘም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 13:6
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔ መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ የመ​ረ​ጣ​ች​ሁኝ አይ​ደ​ለም፤ እን​ድ​ት​ሄዱ፥ ፍሬም እን​ድ​ታ​ፈሩ፥ ፍሬ​አ​ች​ሁም እን​ዲ​ኖር፤ አብ​ንም በስሜ የም​ት​ለ​ም​ኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እን​ዲ​ሰ​ጣ​ችሁ ሾም​ኋ​ችሁ።


የመ​ን​ፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕ​ግ​ሥት፥ ምጽ​ዋት፥ ቸር​ነት፥ እም​ነት፥ ገር​ነት፥ ንጽ​ሕና ነው።


እኔ የተ​መ​ረ​ጠች ወይን፥ ፍጹ​ምም እው​ነ​ተኛ ዘር አድ​ርጌ ተክ​ዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለ​ው​ጠሽ እን​ዴት መራራ የእ​ን​ግዳ ወይን ግንድ ሆንሽ?


ይህ​ንም የማ​ነ​ሣ​ሣው ስጦ​ታ​ች​ሁን ፈልጌ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ና​ንተ ላይ የጽ​ድቅ ፍሬ ይበዛ ዘንድ ፈልጌ ነው እንጂ።


አዝ​መ​ራ​ቸ​ውን ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን በወ​ይን ላይ ፍሬ፥ በበ​ለስ ዛፍ ላይ በለስ የለም፤ ቅጠ​ልም ይረ​ግ​ፋል፤ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ አለ​ፈ​ባ​ቸ​ውም።


እነሆ፥ ምሳር በዛ​ፎች ላይ ተቃ​ጥ​ቶ​አል፤ መል​ካም ፍሬ የማ​ያ​ፈ​ራ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ ይቈ​ር​ጡ​ታል፤ ወደ እሳ​ትም ይጥ​ሉ​ታል።”


አይ​ደ​ለም፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ንስሓ ካል​ገ​ባ​ችሁ ሁላ​ችሁ እንደ እነ​ርሱ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”


በለሷ ግን፦ ጣፋ​ጭ​ነ​ቴ​ንና መል​ካ​ሙን ፍሬ​ዬን ትቼ በዛ​ፎች ላይ እነ​ግሥ ዘንድ ልሂ​ድን? አለ​ቻ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች