ሉቃስ 13:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 እርሱም እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም፤ ዐመፅን የምታደርጉ ሁላችሁ፥ ከእኔ ራቁ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 “እርሱም፣ ‘እላችኋለሁ፤ አላውቃችሁም ከየት እንደ መጣችሁም አላውቅም፤ እናንተ ዐመፀኞች ሁሉ ከእኔ ራቁ’ ይላል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 እርሱም ‘እላችኋለሁ፥ ከየት እንደ ሆናችሁ አላወቅም፤ ዐመፀኞች በሙሉ፥ ከእኔ ራቁ፤’ ይላችኋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 እርሱም እንደገና ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም፤ እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ከእኔ ራቁ!’ ይላችኋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 እርሱም፦ እላችኋለሁ፥ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላወቃችሁም፤ ሁላችሁ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ይላችኋል። ምዕራፉን ተመልከት |