Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 13:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ከዚ​ህም በኋላ፦ በፊ​ትህ በላን፥ ጠጣን፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ያ​ች​ንም አስ​ተ​ማ​ርህ ልትሉ ትጀ​ም​ራ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “እናንተም፣ ‘ከአንተ ጋራ ዐብረን በልተናል፤ ጠጥተናል፤ በአደባባያችንም አስተምረሃል’ ትላላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በዚያን ጊዜም ‘በፊትህ በላን፤ ጠጣንም፤ በአደባባያችንም አስተማርህ፤’ ማለት ትጀምራላችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በዚያን ጊዜ እናንተ፥ ‘ከአንተ ጋር አብረን በልተናል፤ አብረን ጠጥተናል፤ በአደባባያችንም አስተምረሃል’ ትሉታላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በዚያን ጊዜም፦ በፊትህ በላን ጠጣንም በአደባባያችንም አስተማርህ ልትሉ ትጀምራላችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 13:26
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ጽድ​ቅን እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ የአ​ም​ላ​ኩ​ንም ፍርድ እን​ደ​ማ​ይ​ተው ሕዝብ ዕለት ዕለት ይሹ​ኛል፤ መን​ገ​ዴ​ንም ያውቁ ዘንድ ይወ​ድ​ዳሉ። አሁ​ንም እው​ነ​ተ​ኛ​ውን ፍርድ ይለ​ም​ኑ​ኛል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ቅ​ረብ ይወ​ድ​ዳሉ።


እር​ሱም እን​ዲህ ይላ​ቸ​ዋል፦ እና​ንተ ከወ​ዴት እንደ ሆና​ችሁ አላ​ው​ቃ​ች​ሁም፤ ዐመ​ፅን የም​ታ​ደ​ርጉ ሁላ​ችሁ፥ ከእኔ ራቁ፤


እን​ግ​ዲህ ለን​ስሓ የሚ​ያ​በ​ቃ​ች​ሁን ሥራ ሥሩ፤ አብ​ር​ሃም አባ​ታ​ችን አለን በማ​ለት የም​ታ​መ​ልጡ አይ​ም​ሰ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ለአ​ብ​ር​ሃም ልጆ​ችን ማስ​ነ​ሣት እን​ደ​ሚ​ችል እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


የአምልኮት መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።


እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፤ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች