Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 13:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ባለ​ቤቱ ተነ​ሥቶ ደጁን ይዘ​ጋ​ልና፤ ያን​ጊዜ ከደጅ ቆመው፦ ‘አቤቱ፥ አቤቱ፥ ክፈ​ት​ልን’ እያሉ በር ሊመቱ ይጀ​ም​ራሉ፤ መል​ሶም፦ ከወ​ዴት እንደ ሆና​ችሁ አላ​ው​ቃ​ች​ሁም ይላ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 የቤቱ ባለቤት ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ በውጭ ቆማችሁ፣ ‘ጌታ ሆይ፤ በሩን ክፈትልን’ እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ። “እርሱ ግን፣ ‘ማን እንደ ሆናችሁና ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም’ ብሎ ይመልስላችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ባለቤቱ ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ፥ እናንተ በውጭ ቆማችሁ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን’ እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም መልሶ ‘ከየት እንደ ሆናችሁ አላውቅም’ ይላችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 የቤቱ ጌታ ተነሥቶ በሩን ይዘጋዋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ በሩን በማንኳኳት፥ ‘ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ ማለት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም!’ ሲል ይመልስላችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ባለቤቱ ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ፥ እናንተ በውጭ ቆማችሁ፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን እያላችሁ በሩን ልታንኳኩ ትጀምራላችሁ እርሱም መልሶ፦ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም ይላችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 13:25
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሥጋ ካለው ሁሉ የገ​ቡ​ትም ተባ​ትና እን​ስት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኖኅን እን​ዳ​ዘ​ዘው ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መር​ከ​ብ​ዋን በስ​ተ​ውጭ ዘጋት።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሰማ​ዮች ጸኑ፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ በአፉ እስ​ት​ን​ፋስ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ገ​ኝ​በት ጊዜ ፈል​ጉት፤ ቀር​ቦም ሳለ ጥሩት፤


በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል ‘እናንተ ርጉማን! ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።


እር​ሱም እን​ዲህ ይላ​ቸ​ዋል፦ እና​ንተ ከወ​ዴት እንደ ሆና​ችሁ አላ​ው​ቃ​ች​ሁም፤ ዐመ​ፅን የም​ታ​ደ​ርጉ ሁላ​ችሁ፥ ከእኔ ራቁ፤


እን​ግ​ዲህ ለን​ስሓ የሚ​ያ​በ​ቃ​ች​ሁን ሥራ ሥሩ፤ አብ​ር​ሃም አባ​ታ​ችን አለን በማ​ለት የም​ታ​መ​ልጡ አይ​ም​ሰ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ለአ​ብ​ር​ሃም ልጆ​ችን ማስ​ነ​ሣት እን​ደ​ሚ​ችል እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


“ለምን አቤቱ፥ አቤቱ፥ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ? የም​ላ​ች​ሁ​ንም አታ​ደ​ር​ጉም።


እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በተ​መ​ረ​ጠ​ችው ቀን ሰማ​ሁህ፤ በመ​ዳ​ንም ቀን ረዳ​ሁህ” እነሆ፥ የተ​መ​ረ​ጠ​ችው ቀን ዛሬ ናት።


ከዚያ በኋላ እንኳ በረ​ከ​ትን ሊወ​ርስ በወ​ደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና፤ በእ​ን​ባም ተግቶ ምንም ቢፈ​ል​ጋት ለን​ስሓ ስፍራ አላ​ገ​ኘ​ምና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች