Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ይህቺ የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ እነሆ፥ ሰይ​ጣን ከአ​ሰ​ራት ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ነው፤ እር​ስ​ዋስ በሰ​ን​በት ቀን ከእ​ስ​ራቷ ልት​ፈታ አይ​ገ​ባ​ምን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ታዲያ፣ ይህች ሴት የአብርሃም ልጅ ሆና ሳለች ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ በሰይጣን ታስራ ስትኖር፣ ከዚህ እስራት በሰንበት ቀን መፈታት አይገባትምን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ይህች ለዐሥራ ስምንት ዓመት ሰይጣን ያሠራት የአብርሃም ልጅ በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እነሆ፥ የአብርሃም ዘር የሆነች ይህች ሴት ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ በሰይጣን ታስራ ስትሠቃይ ኖራለች፤ ታዲያ፥ እርስዋ ታስራ ከምትሠቃይበት በሽታ በሰንበት ቀን መፈታት አይገባትምን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 13:16
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግሞ “ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤


“እና​ንተ ከአ​ብ​ር​ሃም ወገን የተ​ወ​ለ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈሩ፥ ይህ የሕ​ይ​ወት ቃል ለእ​ና​ንተ ተል​ኮ​አል።


እና​ን​ተስ ከአ​ባ​ታ​ችሁ ከሰ​ይ​ጣን ናችሁ፤ የአ​ባ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈቃድ ልታ​ደ​ርጉ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ከጥ​ንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእ​ው​ነ​ትም አይ​ቆ​ምም፤ በእ​ርሱ ዘንድ እው​ነት የለ​ምና፤ ሐሰ​ት​ንም በሚ​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ከራሱ አን​ቅቶ ይና​ገ​ራል፤ ሐሰ​ተኛ ነውና፤ የሐ​ሰ​ትም አባት ነውና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “ዛሬ ለዚህ ቤት ሕይ​ወት ሆነ፤ እርሱ የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ ነውና።


እን​ግ​ዲህ ለን​ስሓ የሚ​ያ​በ​ቃ​ች​ሁን ሥራ ሥሩ፤ አብ​ር​ሃም አባ​ታ​ችን አለን በማ​ለት የም​ታ​መ​ልጡ አይ​ም​ሰ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮች ለአ​ብ​ር​ሃም ልጆ​ችን ማስ​ነ​ሣት እን​ደ​ሚ​ችል እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


ያን ጊዜ ኢየሱስ “ሂድ፤ አንተ ሰይጣን ‘ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፎአልና” አለው።


‘አባት አብ​ር​ሃም ሆይ፥ እዘ​ን​ልኝ፤ በዚች እሳት እጅግ ተሠ​ቃ​ይ​ቻ​ለ​ሁና፥ ጣቱን ከውኃ ነክሮ ምላ​ሴን ያቀ​ዘ​ቅ​ዝ​ልኝ ዘንድ አል​ዓ​ዛ​ርን ላከው’ ብሎ ተጣራ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች