Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 12:56 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

56 እና​ንት ግብ​ዞች! የሰ​ማ​ዩ​ንና የም​ድ​ሩን ፊት መመ​ር​መር ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን እነ​ዚ​ህን ዘመ​ናት መመ​ር​መ​ርን እን​ዴት አታ​ው​ቁም?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

56 እናንተ ግብዞች፤ የምድሩንና የሰማዩን መልክ መመርመር ታውቁበታላችሁ፤ ታዲያ ይህን የአሁኑን ዘመን መመርመር እንዴት ተሳናችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

56 እናንት ግብዞች! የምድሩንና የሰማዩን ፊት ልትመረምሩ ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን ይህን ዘመን የማትመረምሩ እንዴት ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

56 እናንተ ግብዞች የምድሩንና የሰማዩን መልክ በመመልከት የሚሆነውን ታውቃላችሁ፤ ታዲያ በዚህ በአሁኑ ዘመን የሚሆነውን ለምን አታውቁም?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

56 እናንት ግብዞች፥ የምድሩንና የሰማዩን ፊት ልትመረምሩ ታውቃላችሁ፥ ነገር ግን ይህን ዘመን የማትመረምሩ እንዴት ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 12:56
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እስ​ራ​ኤ​ልም የሚ​ገ​ባ​ውን ያደ​ርግ ዘንድ ዘመ​ኑን የሚ​ያ​ውቁ ጥበ​በ​ኞች ሰዎች የይ​ሳ​ኮር ልጆች አለ​ቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።


አሕዛብን ሁሉ አናውጣለሁ፥ በአሕዛብ ሁሉ የተመረጠውም ዕቃ ይመጣል፣ ይህንም ቤት በክብር እሞላዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።


ማለዳም ‘ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል’ ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፤ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን?


“እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


ነገር ግን ቀጠ​ሮው በደ​ረሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ላከ፤ ከሴ​ትም ተወ​ለደ፤ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ፈጸመ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች