Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 12:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 እና​ን​ተም፥ በመ​ጣና በር በመታ ጊዜ ወዲ​ያው ይከ​ፍ​ቱ​ለት ዘንድ ከሰ​ርግ እስ​ኪ​መ​ለስ ጌታ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቁ ሰዎች ሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ጌታቸው ከሰርግ ግብዣ እስኪመለስ የሚጠባበቁና መጥቶም በር ሲያንኳኳ ወዲያው ለመክፈት ዝግጁ የሆኑ ሰዎችን ምሰሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 በዚህም አኳኋን፥ ጌታቸው ከሠርግ ቤት መመለሱን የሚጠባበቁ አገልጋዮችን ምሰሉ፤ እነርሱ ጌታቸው በድንገት መጥቶ በሩን በሚያንኳኳበት ጊዜ ፈጥነው ለመክፈት ዝግጁዎች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 12:36
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያድ​ነው ዘንድ ይጠ​ብ​ቃል።


ከጥ​ንት ጀምሮ ይቅ​ር​ታ​ህን ለሚ​ጠ​ባ​በቁ ምሕ​ረ​ትን ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ከአ​ንተ በቀር ሌላ አም​ላክ አላ​የ​ንም፤ አል​ሰ​ማ​ን​ምም።


“ወገ​ባ​ችሁ የታ​ጠቀ መብ​ራ​ታ​ች​ሁም የበራ ይሁን።


ጌታ​ቸው በመጣ ጊዜ እን​ዲህ ሲያ​ደ​ር​ጉና ሲተጉ የሚ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አገ​ል​ጋ​ዮች ብፁ​ዓን ናቸው፤ እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወገ​ቡን ታጥቆ በማ​ዕድ ያስ​ቀ​ም​ጣ​ቸ​ዋል፤ እየ​ተ​መ​ላ​ለ​ሰም ያገ​ለ​ግ​ላ​ቸ​ዋል።


የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ፤ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ።


እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች