Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 11:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 የነ​ነዌ ሰዎች በፍ​ርድ ቀን ከዚች ትው​ልድ ጋር ተነ​ሥ​ተው ይፋ​ረ​ዱ​አ​ታል፤ ያሳ​ፍ​ሩ​አ​ታ​ልም፤ ዮናስ በሰ​በ​ከ​ላ​ቸው ጊዜ ንስሓ ገብ​ተ​ዋ​ልና፤ እነሆ፥ ከዮ​ናስ የሚ​በ​ልጥ በዚህ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 የነነዌ ሰዎችም በፍርድ ጊዜ ከዚህ ትውልድ ጋራ ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ እነርሱ የዮናስን ስብከት ሰምተው ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆ፣ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ይነሳሉ፥ በእርሱም ላይ ይፈርዳሉ፤ በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ በዚህ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 እንዲሁም የነነዌ ከተማ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው በእርሱ ላይ ይፈርዱበታል፤ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት በሰሙ ጊዜ በኃጢአታቸው ተጸጽተው ንስሓ ገብተዋል፤ ነገር ግን እነሆ፥ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 የነነዌ ሰዎች በፍርድ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፥ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 11:32
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቅዱ​ስና ያለ ተን​ኰል፥ ነው​ርም የሌ​ለ​በት፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም የተ​ለየ፥ ከሰ​ማ​ያ​ትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሊቀ ካህ​ናት ይገ​ባ​ናል።


የአ​ዜብ ንግ​ሥት በፍ​ርድ ቀን ከዚች ትው​ልድ ጋር ተነ​ሥታ ትፋ​ረ​ዳ​ቸ​ዋ​ለች፤ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ጥበብ ልት​ሰማ ከም​ድር ዳርቻ መጥ​ታ​ለ​ችና፤ እነሆ፥ ከሰ​ሎ​ሞን የሚ​በ​ልጥ በዚህ አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን፥ “በውኑ ስለ​ዚች ቅል ታዝ​ና​ለ​ህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እስ​ክ​ሞት ድረስ እጅግ አዝ​ኛ​ለሁ” አለ።


የነ​ነዌ ሰዎ​ችም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመኑ፤ ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፤ ከታ​ላ​ቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።


ዮና​ስም የአ​ንድ ቀን መን​ገድ ያህል ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፥ “በሦ​ስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገ​ለ​በ​ጣ​ለች አለ።”


እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው “ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፤ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።


የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፤ እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች