Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 10:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፥ ትቸ​ገ​ሪ​ያ​ለ​ሽም፤ ታዘ​ጋ​ጂ​ያ​ለ​ሽም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ጌታ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት፤ “ማርታ፣ ማርታ፤ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትዋከቢአለሽም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ማርታ! ማርታ! በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪያለሽም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ጌታ ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “ማርታ፥ ማርታ፥ አንቺ በብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትታወኪያለሽም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 10:41
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከን​ቱን የሚ​ያ​በዛ ብዙ ነገር አለና፥ ለሰው ጥቅሙ ምን​ድር ነው?


የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፤ የማያፈራም ይሆናል።


ከዚ​ህም በኋላ ሄደው ወደ አን​ዲት መን​ደር ገቡ፤ ማርታ የም​ት​ባል አን​ዲት ሴትም በቤቷ ተቀ​በ​ለ​ችው።


ማርታ ግን ብዙ በማ​ዘ​ጋ​ጀት ትደ​ክም ነበር፤ ቆማም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኅቴ ትታኝ ብቻ​ዬን ስሠራ አያ​ሳ​ዝ​ን​ህ​ምን? ርጃት በላት” አለ​ችው።


ለደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ስለ​ዚህ እላ​ች​ህ​ዋ​ለሁ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ስለ​ም​ት​በ​ሉ​ትና ስለ​ም​ት​ጠ​ጡት፥ ለሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁም ስለ​ም​ት​ለ​ብ​ሱት አት​ጨ​ነቁ።


“ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፤ በመ​ብ​ልና በመ​ጠጥ፥ በመ​ቀ​ማ​ጠ​ልና የዓ​ለ​ምን ኑሮ በማ​ሰብ ልባ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ያቺ ቀንም በድ​ን​ገት ትደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ለች።


በእ​ሾ​ህም መካ​ከል የወ​ደ​ቀው ቃሉን ሰም​ተው የባ​ለ​ጠ​ግ​ነት ዐሳብ፥ የኑ​ሮም መቈ​ር​ቈር የተ​ድ​ላና የደ​ስታ መጣ​ፈ​ጥም የሚ​አ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸ​ውና ፍሬ የማ​ያ​ፈሩ ናቸው።


የማ​ር​ያ​ምና የእ​ኅቷ የማ​ርታ መን​ደር በሚ​ሆን በቢ​ታ​ንያ ስሙ አል​ዓ​ዛር የሚ​ባል የታ​መመ አንድ ሰው ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ማር​ታ​ንና እኅ​ቷን ማር​ያ​ምን፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ይወ​ዳ​ቸው ነበር።


በዚ​ያም ምሳ አደ​ረ​ጉ​ለት፤ ማር​ታም ታሳ​ል​ፍ​ላ​ቸው ነበር፤ አብ​ረ​ውት ምሳ ከበ​ሉ​ትም አንዱ አል​ዓ​ዛር ነበር።


በም​ንም አት​ጨ​ነቁ፤ ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማል​ዱም፤ እያ​መ​ሰ​ገ​ና​ች​ሁም ልመ​ና​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግለጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች