Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 10:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አን​ቺም ቅፍ​ር​ና​ሆም እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ከፍ ብትዪ እስከ ሲኦል ትወ​ር​ጃ​ለሽ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አንቺም ቅፍርናሆም፤ ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ ልትዪ ነውን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ የምትደረጊ ይመስልሻልን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አንቺም ቅፍርናሆም! እስከ ሰማይ ከፍ ለማለት ፈልገሻልን? ታዲያ ወደ ሲኦል ትወርጂአለሽ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 10:15
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።


እግዚአብሔር ኀጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥


አብ​ር​ሃ​ምን፥ ይስ​ሐ​ቅ​ንና ያዕ​ቆ​ብን፥ ነቢ​ያ​ት​ንም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት በአ​ያ​ች​ኋ​ቸው ጊዜ እና​ን​ተን ወደ ውጭ ያወ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ በዚ​ያም ልቅ​ሶና ጥርስ ማፋ​ጨት ይሆ​ናል።


አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና።


ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።


እንደ ንስር መጥ​ቀህ ብት​ወጣ፥ ቤት​ህም በከ​ዋ​ክ​ብት መካ​ከል ቢሆን፥ ከዚያ አወ​ር​ድ​ሃ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በሕ​ያ​ዋ​ንም ምድር ኀያ​ላ​ኑን ያስ​ፈሩ ነበ​ርና፤ መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ወደ ሲኦል ከወ​ረዱ፥ ሰይ​ፋ​ቸ​ው​ንም ከራ​ሳ​ቸው በታች ከአ​ደ​ረጉ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም በአ​ጥ​ን​ታ​ቸው ላይ ከሆነ ጋር ከወ​ደቁ ካል​ተ​ገ​ረዙ ኀያ​ላን ጋር ይተ​ኛሉ።


በሰ​ይፍ በተ​ገ​ደ​ሉት መካ​ከል ከእ​ርሱ ጋር በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ኀይ​ሉም ሁሉ ይጠ​ፋል፤ እር​ስ​ዋ​ንና ብዛ​ቷን ሁሉ ጐትቱ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ኀይል ዋይ በል፤ እር​ስ​ዋ​ንና የብ​ር​ቱ​ዎ​ቹን አሕ​ዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ወደ ታች​ኛው ምድር ጣላ​ቸው።


“በክ​ብ​ርና በታ​ላ​ቅ​ነት በዔ​ድን ዛፎች መካ​ከል ማንን ትመ​ስ​ላ​ለህ? ነገር ግን ከዔ​ድን ዛፎች ጋር ወደ ታች​ኛው ምድር ያወ​ር​ዱ​ሃል፤ በሰ​ይ​ፍም በተ​ገ​ደ​ሉት ባል​ተ​ገ​ረ​ዙት መካ​ከል ትተ​ኛ​ለህ። ይህም ፈር​ዖ​ንና የሕ​ዝቡ ብዛት ሁሉ ነው፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ወደ ጥልቁ ከሚ​ወ​ር​ዱት ጋር ወደ ቀደ​ሙት ሕዝብ አወ​ር​ድ​ሻ​ለሁ። በም​ድ​ርም ላይ በሕ​ይ​ወ​ትሽ ጸን​ተሽ እን​ዳ​ት​ኖ​ሪም ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ሰዎች ጋር ቀድሞ በፈ​ረ​ሰው ቤት ከም​ድር በታች አኖ​ር​ሻ​ለሁ።


ባቢ​ሎ​ንም ወደ ሰማይ ብት​ወጣ፥ ቅፅ​ሮ​ች​ዋ​ንም በኀ​ይ​ልዋ ብታ​ጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥ​ፊ​ዎች ይመ​ጡ​ባ​ታል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሲኦ​ልም ሆድ​ዋን አስ​ፍ​ታ​ለች፤ አፍ​ዋ​ንም ያለ ልክ ከፍ​ታ​ለች፤ የተ​ከ​በ​ሩና ታላ​ላቅ ሰዎች ባለ​ጠ​ጎ​ቻ​ቸ​ውና ድሆ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እር​ስዋ ይወ​ር​ዳሉ።


ወዴት እን​ወ​ጣ​ለን? ሕዝቡ ታላ​ቅና ብዙ ነው፤ ከእ​ኛም ይጠ​ነ​ክ​ራሉ፤ ከተ​ሞ​ቹም ታላ​ላ​ቆች፥ የተ​መ​ሸ​ጉም፥ እስከ ሰማ​ይም የደ​ረሱ ናቸው፤ የረ​ዐ​ይ​ት​ንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየ​ና​ቸው ብለው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ልባ​ች​ንን አስ​ፈ​ሩት።’


እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ኑ ለእኛ ከተ​ማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ግንብ እን​ሥራ፤ በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ሳን​በ​ተን ስማ​ች​ንን እና​ስ​ጠ​ራው” ተባ​ባሉ።


በሲ​ኦ​ልም በሥ​ቃይ ሳለ ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ አብ​ር​ሃ​ምን ከሩቅ አየው፤ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም በአ​ጠ​ገቡ ተቀ​ምጦ አየው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች