Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 10:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “ኮራዚ ወዮ​ልሽ! ቤተ ሳይዳ ወዮ​ልሽ! በእ​ና​ንተ የተ​ደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት በጢ​ሮ​ስና በሲ​ዶና ተደ​ርጎ ቢሆን ቀድሞ ማቅ ለብ​ሰው አመ​ድም ነስ​ን​ሰው በተ​ቀ​መጡ ንስ​ሓም በገቡ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ታምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ፣ ገና ዱሮ ማቅ ለብሰው፣ ዐመድ ነስንሰው ንስሓ በገቡ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ፥ ማቅ ለብሰው በአመድ ላይም ተቀምጠው፥ ገና ድሮ፥ ንስሐ በገቡ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ተአምራት፥ በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የሐዘን ልብስ ለብሰውና ዐመድ ላይ ተቀምጠው፥ ገና ዱሮ ንስሓ በገቡ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ወዮልሽ ኮራዚን፥ ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ፤ በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው በአመድም ተቀምጠው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 10:13
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ​ዚህ ራሴን እን​ቃ​ለሁ፤ ሰው​ነ​ቴም ቀለጠ። እኔ አፈ​ርና አመድ እንደ ሆንሁ አው​ቃ​ለሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለክ​ብሩ የተ​ከ​ላ​ቸው የጽ​ድቅ ዛፎች እን​ዲ​ባሉ ለጽ​ዮን አል​ቃ​ሾች አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በአ​መ​ድም ፋንታ አክ​ሊ​ልን፥ በል​ቅ​ሶም ፋንታ የደ​ስ​ታን ዘይት፥ በኀ​ዘ​ንም መን​ፈስ ፋንታ የም​ስ​ጋ​ናን መጐ​ና​ጸ​ፊያ እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ልኮ​ኛል።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ከወሩ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የሰ​ሎ​ሞን ምር​ኮ​ኞ​ችን በኤ​ዶ​ም​ያስ ዘግ​ተ​ዋ​ልና፥ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ንም ቃል ኪዳን አላ​ሰ​ቡ​ምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢ​ሮስ ኀጢ​አት አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች