Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 1:74 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

74 ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ድነን ያለ ፍር​ሀት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

74 ከጠላቶቻችን እጅ አውጥቶ፣ ያለ ፍርሀት እንድናገለግለው፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

74 በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን ያለ ፍርሃት

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

74 የተስፋውም ቃል ከጠላቶቻችን እጅ ነጻ ወጥተን፥ ያለ ፍርሀት እንድናገለግለው ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

74-75 በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 1:74
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር የኀይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።


ነውር የሌ​ለው ሆኖ፥ በዘ​ለ​ዓ​ለም መን​ፈስ ራሱን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረበ የክ​ር​ስ​ቶስ ደም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ከው ዘንድ ሕሊ​ና​ች​ንን ከሞት ሥራ እን​ዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?


ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፤ ዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።


በሕ​ይ​ወት ዘመ​ና​ቸው ሁሉ ሞትን በመ​ፍ​ራት የተ​ቀ​ጡ​ትን፥ ለባ​ር​ነት የተ​ገ​ዙ​ት​ንም ሁሉ ያሳ​ር​ፋ​ቸው ዘንድ።


ዳግ​መ​ናም አባ አባት ብለን የም​ን​ጮ​ህ​በ​ትን የል​ጅ​ነት መን​ፈስ ተቀ​በ​ላ​ችሁ እንጂ እንደ ገና ለፍ​ር​ሀት የባ​ር​ነት መን​ፈ​ስን አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ምና።


ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ፥ ከሚ​ጠ​ሉ​ንም ሁሉ እጅ ያድ​ነን ዘንድ።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን በዘ​ለ​ዓ​ለ​ማዊ መድ​ኀ​ኒት ያድ​ነ​ዋል፤ እና​ን​ተም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ፍ​ሩ​ምና አቷ​ረ​ዱም።”


ዛሬ ግን ከኀ​ጢ​አት ነጻ ወጣ​ችሁ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም ለጽ​ድቅ አስ​ገ​ዛ​ችሁ፤ ለቅ​ድ​ስ​ናም ፍሬን አፈ​ራ​ችሁ፤ ፍጻ​ሜው ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ነው።


እነ​ር​ሱም ምስ​ጋ​ና​ዬን እን​ዲ​ና​ገሩ ለእኔ የፈ​ጠ​ር​ኋ​ቸው ሕዝብ ናቸው፤


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፣ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።


ለአ​ባ​ታ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ለ​ውን መሐላ ያስብ ዘንድ።


በቅ​ድ​ስ​ናና በጽ​ድቅ በፊቱ በዘ​መ​ና​ችን ሁሉ እን​ድ​ና​መ​ል​ከው ይሰ​ጠን ዘንድ።


ነገር ግን አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩ፤ እር​ሱም ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸሁ ሁሉ እጅ ያድ​ና​ች​ኋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች