Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 1:67 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

67 በአ​ባቱ በዘ​ካ​ር​ያ​ስም መን​ፈስ ቅዱስ መላ​በት፤ እን​ዲ​ህም ብሎ ትን​ቢት ተና​ገረ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

67 የሕፃኑም አባት ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

67 አባቱ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ትንቢት ተናገረ፤ እንዲህም አለ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

67 የሕፃኑ አባት ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

67 አባቱ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ ሞላበትና ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 1:67
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ መን​ፈ​ሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራሉ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ች​ሁም ራእ​ይን ያያሉ፤


ኤል​ሳ​ቤ​ጥም የማ​ር​ያ​ምን ሰላ​ምታ በሰ​ማች ጊዜ ፅንሱ በማ​ኅ​ፀ​ንዋ ዘለለ፤ በኤ​ል​ሣ​ቤ​ጥም መን​ፈስ ቅዱስ መላ​ባት።


እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታላቅ ይሆ​ና​ልና የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ ሁሉ አይ​ጠ​ጣም፤ ከእ​ናቱ ማሕ​ፀን ጀም​ሮም መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​በ​ታል።


ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፤ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእኔ ተና​ገረ፤ ቃሉም በአ​ን​ደ​በቴ ላይ ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መ​ናው ወረደ፤ ተና​ገ​ረ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ላይ ከነ​በ​ረው መን​ፈስ ወስዶ በሰ​ባው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ላይ አደ​ረገ፤ መን​ፈ​ሱም በላ​ያ​ቸው ባደረ ጊዜ ትን​ቢት ተና​ገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን አል​ተ​ጨ​መ​ረ​ላ​ቸ​ውም።


ሁሉም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተሞሉ፤ ይና​ገሩ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እንደ አደ​ላ​ቸው መጠ​ንም እየ​ራ​ሳ​ቸው በሀ​ገሩ ሁሉ ቋንቋ ይና​ገሩ ጀመሩ።


እን​ግ​ዲህ በየ​ሀ​ገ​ራ​ችን ቋንቋ ሲና​ገሩ እን​ዴት እን​ሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለን?


ያን​ጊ​ዜም ሐና​ንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁ​ንም ጫነ​በ​ትና፥ “ወን​ድሜ ሳውል፥ በመ​ን​ገድ ስት​መጣ የታ​የህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ታይና መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​ብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮ​ኛል” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች