Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 1:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 ኀያ​ላ​ኑን ከዙ​ፋ​ና​ቸው አዋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ትሑ​ታ​ኑ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ረ​ጋ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 ገዦችን ከዙፋናቸው አውርዷቸዋል፤ ትሑታንን ግን ከፍ ከፍ አድርጓቸዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 ገዥዎችን ከዙፋናቸው አውርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 ታላላቅ ገዢዎችን ከዙፋናቸው አውርዶአቸዋል፤ ዝቅተኞችን ግን በክብር ከፍ አድርጎአቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 1:52
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የዱር ዛፎች ሁሉ፥ ረዥ​ሙን ዛፍ ዝቅ ያደ​ረ​ግሁ፥ አጭ​ሩ​ንም ዛፍ ከፍ ያደ​ረ​ግሁ፥ የለ​መ​ለ​መ​ው​ንም ዛፍ ያደ​ረ​ቅሁ፥ የደ​ረ​ቀ​ው​ንም ዛፍ ያለ​መ​ለ​ምሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገ​ርሁ፤ እኔም አደ​ረ​ግሁ።”


በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፤ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ርድ ይከ​ብ​ራ​ልና።”


በመ​ን​ግ​ሥቱ ችግ​ረኛ ቢሆ​ንም ከግ​ዞት ቤት ለመ​ን​ገሥ ወጥ​ቶ​አ​ልና።


የኀ​ያ​ላ​ንን ቀስት ሰብ​ሮ​አል፤ ደካ​ሞ​ች​ንም ኀይ​ልን አስ​ታ​ጥ​ቋ​ቸ​ዋል።


“በዚያ ቀን የወ​ደ​ቀ​ች​ውን የዳ​ዊ​ትን ቤት አነ​ሣ​ለሁ፤ የተ​ና​ደ​ው​ንም ቅጥ​ር​ዋን እጠ​ግ​ና​ለሁ፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም አድ​ሳ​ለሁ፤ እንደ ቀደ​መ​ውም ዘመን እሠ​ራ​ታ​ለሁ፤


ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን?” አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር።


ራሱን ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም ያሚ​ያ​ዋ​ርድ ከፍ ይላ​ልና።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች